1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢዉ ሰላምና የደህንነት እጦት በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 26 2014

ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔረሰብ ማንነትን እና ዘርን እንዲሁም ኃይማኖትን መነሻ ያደረጉ ጥቃቶችና ግጭቶች ውለው ካደሩ የአገሪቱ ችግሮች ጋር ተዳምረው የሰላምና የደኅንነት ስጋትን እንዲባባሱ እያደረጉት ይገኛል። በኢትዮጵያ ውስጥ በልዩነት ላይ የተመሠረቱ ተቋማት መኖራቸው እና ባሉበት መቀጠላቸው ሌላዉ ትልቁ ችግር ነዉ።

https://p.dw.com/p/4ApAj
Karte Sodo Ethiopia ENG

በልዩነት ላይ የተመሠረቱ ተቋማት መኖራቸው ትልቁ ችግር ነዉ

በኢትዮጵያ ውስጥ በልዩነት ላይ የተመሠረቱ ተቋማት መኖራቸው እና ባሉበት መቀጠላቸው አገሪቱ የሰላምና የደኅንነት ቀውስ ውስጥ እንድትወድቅ ማድረጉን አንድ የዘርፉ ተንታኝ ተናገሩ።ሌላ የሕግ ባለሞያ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ የተጠያቂነት አለመኖር፣ በብሔር ማንነት ላይ የሚታይ ልዩነትና የተካረረ ግንኙነት ብሎም የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የፖለቲካ ቁርጠነት ማነስ ወደፊት ከዚህ የባሰ የሰላም መናጋት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔረሰብ ማንነትን እና ዘርን እንዲሁም ኃይማኖትን መነሻ ያደረጉ ጥቃቶችና ግጭቶች ውለው ካደሩ የአገሪቱ ችግሮች ጋር ተዳምረው የሰላምና የደኅንነት ስጋትን እንዲባባሱ እያደረጉት ይገኛል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ