1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አምነስቲ የኢትዮጵያ የሃሳብ ነፃነት መሸርሸር አሳስቦኛል አለ 

ሰኞ፣ መስከረም 26 2012

ኢትዮጵያዉስጥ ታይቶ የነበረዉ የኃሳብ ነፃነት እየተሸረሸረ መሆኑ አሳስቦኛል ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለፀ። ድርጅቱ ይህን ያለዉ «ቄሮ ቢሊሱማ በተባለ ቡድን ዉስጥ የሚሰሩ ሦስት ጋዜጠኞችና ሁለት ጓደኞቻቸዉ ሽብርተኝነትን በማነሳሳት ወንጀል ተከሰዉ መታሰራቸዉን ተከትሎ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3QqcB
Logo von Amnesty International

ጋዜጠኞቹ በሽብርተጠረጠሩ እንጂ ፖሊስ ለምን እንደጠረጠራቸዉ መግለጽ አልቻለም


ኢትዮጵያዉስጥ ታይቶ የነበረዉ የኃሳብ ነፃነት እየተሸረሸረ መሆኑ አሳስቦኛል ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለፀ። ድርጅቱ ይህን ያለዉ «ቄሮ ቢሊሱማ በተባለ ቡድን ዉስጥ የሚሰሩ ሦስት ጋዜጠኞችና ሁለት ጓደኞቻቸዉ ሽብርተኝነትን በማነሳሳት ወንጀል ተከሰዉ መታሰራቸዉን ተከትሎ ነዉ። ጋዜጠኞቹ  በሽብርተኝነት ተጠረጠሩ ተባለ እንጂ ፖሊስ ለምን እንደጠረጠራቸዉ መግለጽ አለመቻሉን ድርጅቱ ገልጾአል። ብዙ ችግር ያለበት የኢትዮጵያ የፀረ ሽብር አዋጅ መብትን የሚጥስ ነዉ ሲል መንግሥት ማመኑንንም ድርጅቱ አስታዉሷል ። በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪቃ አጥኚ አቶ ፍስሃ ተክሌን ስለታሰሩት ጋዜጠኞች ጉዳይ ጠይቀናቸዋል።   


አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ