1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አምነስቲ ስለማይካድራዉ ጭፍጨፋ ማስረጃ ደርሶኛል አለ 

ዓርብ፣ ኅዳር 4 2013

በምዕራባዊ ትግራይ  ሁመራ አቅራቢያ “ማይካድራ” በተባለ አካባቢ የህወሓት ልዩ ኃይል ባልታጠቁ ዜጎች ላይ አሰቃቂ እልቂት መፈፀሙን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ። ድርጅቱ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ፤ ሲቪል ነዋሪዎች የተገደሉት በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ በህወሓት ታማኝ ኃይሎች ነዉ።

https://p.dw.com/p/3lHEf
Logo von Amnesty International

የተመድ «የጅምላ ጭፍጨፋዉ የጦር ወንጀል ስለሞኑ መጣራት አለበት»

በምዕራባዊ ትግራይ  ሁመራ አቅራቢያ “ማይካድራ” በተባለ አካባቢ የህወሓት ልዩ ኃይል ባልታጠቁ ዜጎች ላይ አሰቃቂ እልቂት መፈፀሙን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ። ድርጅቱ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ፤ ሲቪል ነዋሪዎች የተገደሉት በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ በህወሓት ታማኝ ኃይሎች ነዉ። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት  ሁመራን ከተቆጣጠረ በኋላ በቀጣይ ወደ ማይካድራ እያመራ ባለበት ወቅት፤  ኅዳር 1/2013 ዓ.ም ንጋት ላይ የህወሓት ኃይል በአገር መከላከያ ሠራዊት ቦታዉ ላይ ከመድረሱ በፊት በአካባቢው ላይ የነበሩ የአማራ ተወላጅ የቀን ሰራተኞችን ከሌሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ በየቤታቸው እየገባ በተኙበት በግፍ የገደለዉ። አምነስቲ የግፍ ጭፍጨፋዉ በአማራ ላይ የተካሄደ መሆኑን የሚያመላክት ነገር እንዳለዉ ገልፆአል። 


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ