1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ አፍሪቃ ሃገራት በገዳይ የኮሌራ ወረርሺኝ ተመቱ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 12 2016

በደቡብ አፍሪቃ ከዐሥር ዓመት ወዲህ የተስፋፋው የኮሌራ ወረርሺኝ በዋናነት ዛምቢያ፤ ዚምባብዌ እና ማላዊን አጥቅቷል ። ወረርሺኙን ለመቅለበስ የነበረው የክትባት ክምችትም እየተሟጠጠ ነው ።

https://p.dw.com/p/4ezHt
Malawi Cholera-Epidemie
ምስል Thoko Chikondi/AP Photo/picture alliance

በአፍሪቃ በኮሌራ ወረርሺኝ በብርቲ የተመቱት ሃገራት

የኮሌራ ወረርሺኝ የደቡብ አፍሪቃ ሃገራትን ከዐሥር ዓመት ወዲህ በብርቱ መምታቱ ተዘግቧል ። የዶይቸ ቬለዋ ኬት ሐሪሰን ዘገባ አላት ። በዛሬው የትኩረት በአፍሪቃ መሰናዶዋችን ቀዳሚው አድርገነዋል ።  ካለፉት አራት ወራት ወዲህ በደቡባዊ የአፍሪቃ ሃገራት ከ1,000 በላይ ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸውን አጥተዋል ። በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በብርቱው ገዳይ የኮሌራ ወረርሽኝ ተጠቅተዋል ። በረረሺኙ እጅግ የተጎዱት ሃገራት፦ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ከበደቡብ አፍሪካቃ ሃገራት ሞዛምቢክ፣ ዚምባብዌ እና ዛምቢያ ናቸው ። ወደ ሰሜን ሲል ደግሞ ኮሌራ በኢትዮጵያም ጉዳት አድርሷል

በከፍተኛ ሁኔታ ተላላፊ ከሆነው የኮሌራ በሽታ ባክቴሪያ ጋ ንክኪ ሲፈጠር በሰዓታት ውስጥ ከባድ ተቅማጥ እና የሰውነት ድርቀት ይከተላል ። ባክቴሪያው አግኝቷቸው በፍጥነት ከታከሙ ሰዎች መካከል ለሞት የሚዳረጉት ከአንድ ከመቶ በታች ናቸው። ። ነገር ግን ከዓለም ድሃ ሃገራት መካከል አንዷ በሆነችው ዛምቢያ የሟቾች ቁጥር ከ3 ከመቶ በላይ ነው ።  ሰዎች በጎስቋላ መንደሮች ተፋፍገው በድህነት ከሚኖሩባቸው ሃገራት አንዷ በሆነችው ዛምቢያ ከአምስት ወራት በፊት ወቅታዊ ዝናብ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ740 በላይ በኮሌራ ወረርሺኝ የተነሳ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ተመዝግቧል ።

«ኮሌራን በተመለከ እጅግ አሳሳቢው ገጉዳይ በሽታው ሰዎችን በያዘ በሰአታት ውስጥ ሊገድል መቻሉ ነው ሰዎች ካልታከሙ እና እንክብካቤ ካላገኙ 3 እስከ 4 ቢበዛ 24 ሰአት ውስጥ ሊሞቱ ይችላሉ በሁለተኛ ደረጃ፦ የኮሌራ ወረርሺኝ ሥርጭት በከተሞች በተለይ ደካማ የንፅሕና አጠባበቅ እና የውኃ አቅርቦት ባለባቸው አካባቢዎች እጅግ ፈጣን ነው »

ኮሌራ እንዴት ነው የሚዛመተው?

ኮሌራ በአብዛኛው የሚስፋፋው  በተፈጥሮ አደጋ በተጎዱ አካባቢዎች ነው ። በማአከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የባንጉዊ የአርብቶ አደሮች ተቋማ ኃላፊ እና የተላላፊ በሽታዎች አጥኚ ያፕ ቦም በተፋፈጉ ጎስቋላ መንደሮች ውስጥ መኖር ለወረርሺኙ መስፋፋት ዋነኛ ሰበብ መሆኑንም አክለዋል ።

«መጸዳጃ ቤቱ ከመጠጥ ውኃ ጉድጓዱ እጅግ ቅርብ የሆነ አንድ መኖሪያ ቤትን እስኪ በምናባችሁ ሳሉ በመጸዳጃ ቤቶቹ እና በመጠጥ ውኃ አቅርቦቱ ላይ በቀላሉ የባክቴሪያው ንክኪ ይኖራል እንዳውም የተለመደው ነው በርካታ ሰዎች ተፋፍገው ወደሚኖሩባቸው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች አለያም በጎርፍ አደጋ ወደተሰጠኩ አባቢዎች ብትሄዱ የመጠጥ ውኃው በኮሌራ በሽታ አማጩ የቪቢሮ ባክቴሪያ እጅግ የተበከለ ነው »

የኮሌራ በሽታ አማጩ የቪቢሮ ባክቴሪያ
የኮሌራ በሽታ አማጩ የቪቢሮ ባክቴሪያ ምስል Dr.Gary Gaugler/OKAPIA/picture-alliance

በአፍሪቃ የኮሌራ ወረርሺኝ መስፋፋትን የሚያባብሱት ምንድን ናቸው?

በብዙ የአፍሪቃ ሃገራት የኮሌራ ወረርሺን በፍጥነት እንዲዛመት የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች አሉም ይላሉ የጤና ባለሞያው ። 

«ኮሌራ በአብዛኛው ለግጭት፣ ለፀጥታ እጦት እና ለድህነት በተጋለጡ ሃገራት የፍትሐዊነት እጦት ምልክት ነው   ምክንያቱም ኮሌራ በተመሳሳይ መልኩ ምእራባውያን ሃገራት ላይ ቢከሰት ከፍተኛ ክትባት አላቸው ጉዳዩ እዚህ እጅግ ተለየ ነው »

የጤና ባለሞያው የዘረዘሯቸው ምክንያቶች በአሁኑ ጊዜ ከኮሌራ ወረርሺኝ ጋ ግብግብ በገጠሙት በእያንዳንዱ የአፍሪቃ ሃገራት ውስጥ ይገኛሉ ።

ሌላኛው ምክንያት ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ ነው ። 

ዙምባብዌ ኮሌራን እየታገለች ነው

በደቡብ አፍሪቃ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት አንያ ዱ ፕሌሲስ በዶይቸ ቬለ ተጠይቀው፦ «ከአየር ንብረት ለውጥ በተገናኘ በየጊዜው የሚጨምረው የከፋ የጎርፍ መጥለቅለቅ [በኮሌራ ወረርሽኞች ላይ] ተጽእኖ አለው» ሲሉ ጽፈዋል። ቀጣናው በአሁኑ ወቅት እያጋጠመው ባለው የዝናብ ወቅት የተነሳ ኮሌራ በብዛት ይከሰታልም ሲሉ በጽሑፍ ምላሽ ሰጥተዋል ።

የኮሌራ ክትባትን በተመለከተስ?

ነገሩን የበለጠ የከፋ የሚያደርገው ደግሞ የኮሌራ ወረርሺኝን ለመከላከል የሚያግዙ ክትባቶች መሟጠጣቸው ነው ። ደቡብ ኮሪያ ውስጥ የሚገኝ አንድ የመድኃኒት ፈብራኪ ኩባንያ በአፍ የሚሰጥ የኮሌራ መከላከያ ክትባትን በአሁኑ ወቅት በብቸኝነት ያመርታል ። ኩባንያው በሳምንት 700,000 ብልቃጥ ክትባቶችን ለገበያ ያቀርባል ። የመድኃኒት ፍላጎቱ ግን ከኩባንያው አቅም በላይ አራት እጥፍ መድረሱን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን መረጃ  (MSF)ይጠቁማል ። 

በሕጻንነት ወቅት ከሚሰጠው የተለመደ የጸረ ኮሌራ ክትባት በተለየ መልኩ ወረርሺኙ ሲከሰት የሚመረተው በልዩ ትእዛዝ ነው ። የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች መድኃኒቶች በተፈለጉ ቁጥር ወዲያው ያመርታሉ ማለት አይደለም ። በዚያ ላይ የአምራቾቹ ፍላጎት ከአንዱ የሌላኛው የተለያየ ነው ። በደቡብ አፍሪቃ ኬፕ ታውን ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪቃ ክትባት ተቋም የክትባት ባለሞያዋ ኤዲና አምፖንሻ የራስን አቅም የማጎልበት ወሳኝነትንያሰምሩበታል ።

«በሽታዎች በሁሉም የዓለም ክፍሎች በተመሳሳይ መልኩ ቅድሚያ አይሰጣቸውም የማምረት አቅምህን በተለይ የኮሌራ በሽታ ወረርሺኝ በከፋ ሁኔታ በተከሰተባቸው የዓለማችን ክፍሎች ብታጎለብት፤ ማለት ሃገራት የባለቤትነት ኃላፊነቱን በመውሰድ በራሳቸው አቅም በመመስረት  የጤና መርኃ-ግብራቸውን በተሻለ ሁኔታ መደገፍ ይችላሉ ማለት ነው »

በአፍሪቃ የተለያዩሃገራት ኮሌራ ጉዳት አድርሷል
በአፍሪቃ የተለያዩሃገራት የኮሌራ ወረርሺኝ ጉዳት አድርሷልምስል JEKESAI NJIKIZANA/AFP/Getty Images

ለመሆኑ ግን ኮሌራ ወረርሺኝን ለመከላከል ክትባት ብቻ ነው መፍትኄው?

የኮሌራ መከላከያ ክትባት ምርት ባለፉት ዐሥር ዓመታት እጅግ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል ።

እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2013 ዓ.ም ሁለት ሚሊዮን  ብልቃጥ የነበረው የክትባት ምርት በ2022 ወደ 36 ሚሊዮን ብልቃጦች ግድም ክምችት ከፍ ብሏል ። እንዲያም ሆኖ ይህ መጠን አሁን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁጥሩ ከፍ ያለውን የኮሌራ ወረርሺኝለመከታተል በቂ አይደለም ። ኤዲና አምፖንሻ ያክላሉ ።

«የኮሌራ መከላከያ ክትባቶችን የምንጠቀመው ወረርሺኙ ሲከሰት በሽታው እንዳይዛመት ለመጠነ ሰፊ የመከላከል ዘመቻ ነው ማለት የምናመርተው ለተወሰኑ ሃገራት የተወሰነ መጠን ነው »

የኮሌራ ክትባት በአፍ ሲሰጥ
የኮሌራ ክትባት በአፍ ሲሰጥምስል Jekesai Njikizana/AFP

ክትባት በሽታን ለመዋጋት ከሚረዱ በርካታ መሣሪያዎች ውስጥ አንዱ ብቻ መሆኑንም ባለሞያዎቹ ይጠቁማሉ ። ይልቁንም ከክትባት ባሻገር ሃገራት እንደ የማኅበረሰብ ጤና ነክ የሆኑ ሌሎች የወረርሺኙ መከላከያዎች ጉዳዮች ላይ ቢያተኩሩም ይመክራሉ ። ኅብረተሰቡ የመጠጥ ውኃን አፍልቶ እንዲጠቀም፤ ጥሩ የንጽሕና አጠባበቅ እንዲኖረው ትምህርት መስጠቱ ላይ ሊተኮርም ይገባል ይላሉ ። ቀላል የሚመስሉ ግን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ልማዶችን ማለትም፦  እጅን መታጠብ፣ ንጹሕ እና አስተማማኝ የውኃሃ ምንጮች አቅርቦቶችን ማሳደግ፤ እንዲሁም የውኃ ጥራት ምርመራ እና ክትትልን ማጎልበት ልብ ሊባልበት እንደሚገባም ጠቁመዋል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ/ኬት ሐሪሰን

ኂሩት መለሠ