1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

አሜሪካ፦የ9/11 ጥቃት እና ያስከተለው ውጥንቅጥ

ሰኞ፣ መስከረም 3 2014

በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም በአሜሪካ የተፈጸመው እና 3, 000 ገደማ ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት መታሰቢያ ባለፈው ቅዳሜ ተካሒዷል። ጥቃቱ በአሜሪካ ካደረሰው የከፋ ጉዳት ባሻገር በሽብር ላይ ለተጀመረው ዓለም አቀፍ ዘመቻ በር ከፍቷል። በአፍጋኒስታን እና በኢራቅ ብርቱ ጦርነት የቀሰቀሰውም ይኸው ጥቃት ነበር።

https://p.dw.com/p/40GHf
USA New York Anschlag auf das World Trade Center
ምስል picture-alliance/AP Photo/C. Soi Cheong

አሜሪካ፦የ9/11 ጥቃት እና ያስከተለው ውጥንቅጥ

አሜሪካ ባለፈው ቅዳሜ በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም የተፈጸመውን እና 3, 000 ገደማ ሰዎች የተገደሉበትን የሽብር ጥቃት አስባ ውላለች። በኒው ዮርክ ከተማ የጥቃቱ ፈጻሚዎች ባገቷቸው አውሮፕላኖች የወደሙት የዓለም የንግድ ማዕከል መንትያ ሕንፃዎች ይገኙ በነበረበት የማንሐታን አካባቢ በተካሔደው የመታሰቢያ መርሐ-ግብር ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች ባራክ ኦባማ እና ቢል ክሊንተን ተገኝተዋል። 

በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በሽብር እና አሸባሪዎች ላይ ጦርነት ያወጁት ከዚህ ጥቃት በኋላ ነበር። ጥቃቱ በአሜሪካ ላይ ካደረሰው ጉዳት ባሻገር በአፍጋኒስታን እና በኢራቅ የጦርነት መነሾ ሆኗል። በዛሬው የማሕደረ ዜና መሰናዶ  ገበያው ንጉሴ ከ20 አመታት በፊት የተፈጸመው ጥቃት እና ጥቃቱን የተከተለውን ውጥንቅጥ ይቃኛል። 

ገበያው ንጉሴ 
እሸቴ በቀለ