1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

አሜሪካ ከአፍጋኒስታን ጦር ጨርሳ አስወጣች

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 25 2013

ዩናይትድ ስቴትስ በአፍጋኒስታን አሰማርታቸዉ የነበሩትን የመጨረሻዎቹን ወታደሮች ከካቡል አውሮፕላን ማረፊያ በማስወጣት በሃገሪቱ ወደ 20 ዓመታት የዘለቀዉን ወታደራዊ ስምሪት በይፋ ማቆሟን አሳወቀች።

https://p.dw.com/p/3zkDE
Afghanistan | US Militärflugzeug am Flughafen Kabul
ምስል Aamir Qureshi/AFP

ዩናይትድ ስቴትስ በአፍጋኒስታን አሰማርታቸዉ የነበሩትን የመጨረሻዎቹን ወታደሮች ከካቡል አውሮፕላን ማረፊያ በማስወጣት በሃገሪቱ ወደ 20 ዓመታት የዘለቀዉን ወታደራዊ ስምሪት በይፋ ማቆሟን አሳወቀች። በአፍጋኒስታን ሰዓት አቆጣጠር ትናንት ለዛሬ አጥብያ እኩለ ለሊት ሊሆን አንድ ደቂቃ ጉዳይ ሲቀረዉ የካቡልን አዉሮፕላን ማረፍያ የለቀቀዉ የአሜሪካን የጦር አዉሮፕላን፤ የመጨረሻዎቹን የአሜሪካ ወታደሮች አሳፍሮ ነዉ ነዉ የወጣዉ። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆባይደን በአፍጋኒስታን ተሰማርተዉ የነበሩ የሃገራቸዉን ወታደሮች ዛሬ ማክሰኞ ጨርሰዉ እንደሚወጡ ቀነ -ገደብ አስቀምጠዉ ነበር። ይሁንና ትዉልደ አፍጋኒስታን የአሜሪካ ዜጎች አሁንም ገና ጨርሰዉ አለምዉጣታቸዉ ተመልቶአል። በስምሪት ላይ የነበሩት የመጨረሻዎቹ የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን መዉጣታቸዉን ተከትሎ የታሊባን ታጣቂዎች መዲና ካቡል ላይ የሩምታ ተኩስን በማሰማት ደስታቸዉን መግለፃቸዉም ተያይዞ ተዘግቦአል። አንድ የታሊባን ቃል- አቀባይ በትዊተር ገፁ ላይ ይፋ እንዳደረገዉ «አፍጋኒስታን አሁን ሙሉ ነፃነትዋን አግኝታለች»

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ