1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአግዋ የቀረጥ ነፃ ንግድ የመሰረዝ ስጋት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 4 2014

ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ተባብሶ ለቀጠለው ግጭት መልስ ለመስጠት የምጣኔ ሐብት ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን በማጤን ላይ እንደምትገኝ ማስታወቋን ተከትሎ በአገሪቱ የእንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የስጋት ድባብ እየጣለበት ይገኛል።

https://p.dw.com/p/41frw
Äthiopien Hawassa Industrial Park
ምስል AFP/E. Jiregna

በአገሪቱ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የስጋት ድባብ አንዣቦአል

ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ተባብሶ ለቀጠለው ግጭት መልስ ለመስጠት የምጣኔ ሐብት ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን በማጤን ላይ እንደምትገኝ ማስታወቋን ተከትሎ በአገሪቱ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የስጋት ድባብ እየጣለበት ይገኛል።

የማዕቀብ ውሳኔው ገቢራዊ ከሆነ የአሜሪካ መንግስት በሰጠው ከቀረጥ ነፃ የንግድ ማበረታቻን መጠቀም ወደ ኢትዮጲያ የገቡ የውጭ ኩባንያዎችንና በእንዱስትሪዎቹ ተቀጥረው የሚሰሩ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ሊጎዳ እንደሚችል ከወዲሁ እየተነገረ ይገኛል።

 

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ  

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ