አማራጭ ማዳበሪያ
ዓርብ፣ ግንቦት 5 2014ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባዉ የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ እየጨመረ፣ በአቅርቦቱም እየቀነሰ መምጣቱ የምርቱ ተጠቃሚዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲያማትሩ እያስገደዳቸው ነዉ፡፡የማደበሪያ መወደድ ወይም እጥረት በቅርቡ ሥራውን ለጀመረው የሀዋሳ ቆሻሻን መልሶ የመጠቀም ማምረቻ ማዕከል ወይም wast recycling plant መልካም የገበያ አጋጣሚን የፈጠረለት ይመስላል፡፡የማምረቻ ማዕከሉ የጎበኘዉ የሐዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ አምራችና ተጠቃሚዎችን አነጋግሯል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ