አማራ ክልል የማሕፀን ካንሰር መከላከያ ክትባት
ሐሙስ፣ የካቲት 25 2013ማስታወቂያ
አማራ ክልል የማሕፀን ካንሰር መከላከያ ክትባት
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ካለፈዉ ጥር ጀምሮ ከግማሽ ሚሊዮን ለሚበልጡ ታዳጊ ልጃገረዶች የማሕፀን ጫፍ ነቀርሳ (ካንሰር) መከላከያ ክትባት መስጡትን አስታወቀ።የቢሮዉ ኃላፊዎች እንዳሉት ክትባቱ የተሰጠዉ ከ9ኝ እስከ 14 ዓመት ለሆናቸዉ ልጃገረዶች ነዉ። ከግማሽ ሚሊዮን ከሚበልጡት ልጃገረዶች ገሚሱ ለሁለተኛ ዙር የተከተቡ ሲሆን የተቀሩት ክትባቱን ሲወስዱ የመጀመሪያቸዉ ነዉ።የማሕፀን ጫፍ ነቀርሳ በርካታ ሴቶችን የሚገድል ደዌ ነዉ።የጤና ባለሙያዎች እንደሚመክሩት በሽታዉን ለመከላከል አንዲት ሴት ሁለቴ መከተብ አለባት።ክትባቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሰጥት ከጀመረ 2 ዓመቱ ነዉ።የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነዉ መኮንን ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
አለምነው መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ