1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ታሪክ

የባውሌ አይቮሪኮስታውያን እናት

Julien Adayé
ሐሙስ፣ ኅዳር 3 2013

ንግሥት አብላ ፖኮው በአሻንቲ ሥርወ መንግሥት የተወለዱ አንዲት ልዕልት ናቸው።ዛሬ እኝህ ንግሥት በኮት ዲቯር «የባውሌ ሕዝብ እናት» ለመባል የበቁ ጠንካራ እና ተወዳጅ ንግሥት ሆነው ይታወሳሉ።

https://p.dw.com/p/3l8jg
African Roots | Abla Pokou

በአሻንቲ የዘር ሀረግ የአብላ ፖኮው ሚና ምን ነበር?

አብላ ፖኮው የተወለዱት በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው። አጎታቸው ኦሳይ ቱቱ ይባላሉ  — በዛሬይቷ ጋና ውስጥ የሚገኘው የአሻንቲ ሥርወ መንግሥትን አብረው የመሠረቱ ንጉስ ናቸው። ንጉሱ ሲሞቱም ስልጣን ለመቆናጠጥ በተደረገ ሹኩቻ ከዙፋኑ ወራሾች አንዱ የሆኑት ዳካን ማለትም የአብላ ፖኩኦ ወንድም ህይወት ያልፋል። የራሳቸው እና የቤተሰባቸው ህይወት ያሰጋቸውም አብላ ፖኮው ሁሉን ትተው ይሰደዳሉ።

አብላ ፖኮው ሲሰደዱ ማን አጀባቸው?
አብላ ፖኮው ለዳኮን ታማኝ ከነበሩ እና ኦፖኩአን ዙፋኑ ላይ ለማየት አሻፈረኝ ካሉ ሰዎች ጋር በሙሉ ሆነው ነበር የተሰደዱት። በርካታ ተከታዮቻቸውንም አሰባስበው ወደ አሁኗ ኮት ዲቫር ነበር ያቀኑት። 

African Roots | Abla Pokou

አብላ ፖኮው እንዴት ወደ ኮት ዲቫር ሊጓዙ ቻሉ?
አንደ አፈ ታሪኩ ከሆነ ንግሥት አብላ ፖኮው እና ተከታዮቻቸው በጎዞ ላይ ሳሉ ከኮሞ ወንዝ ዳርቻ ይደርሱና መሻገር ያቅታቸዋል። የኮሜ ወንዝ የዛሬዎቹን ጋና እና ኮት ዲቫር የሚለይ ተፈጥሮአዊ ድንበር ነው። 

ከባድ ዝናብ በመዝነቡም ምክንያት ወንዙ በከፍተኛ ሁኔታ ሞልቶ ነበር። ስለሆነም በምንም አይነት ሁኔታ ይህንን ማቋረጥ የማይታሰብ ሆነባቸው። አሁንም አፈ ታሪክ እንደሚለው አብላ ፖኮው አብረዋቸው ያሉ እና አዋቂ የሚባሉ አንድ ሰው ጠየቁ ። ሰውየውም ንግሥቲቱ እና ህዝባቸው ውኃውን እንዲሻገሩ ወንዙ ወንድ ህፃን ልጃቸውን መስዋት እንዲያደርጉ እንደሚጠይቅ ነገሯቸው። አብላ ፖኮውም ልጃቸውን ወንዙ ውስጥ ወርውረው ሰምጦ ይሞታል። 

አሁን ድረስ የተለያዩ አፈ ታሪኮች ይነገራሉ። ለምሳሌ ለማመን በሚያዳግት ሁኔታ በወንዙ አቅራቢያ የነበሩ ዛፎች ግንዶቻቸውን አስጎንብሰው ድልድይ ሰርተው እንደነበር ይነገራል። ሌላው ታሪክ ደግሞ ትላልቅ ጉማሬዎች ጎን ለጎን ተሰልፈው እንደ ድልድይ አሳልፈዋቸዋል ይባላል።   

ያም ሆነ ይህ አብላ ፖኮው ወንዙን ተሻግረው በሌላኛው ዳርጃ እንደደረሱ አይናቸው በእንባ ተውጦ "Bâ wouli" እያሉ ያለቅሳሉ። ትርጓሜውም ህፃኑ ሞቷል እንደ ማለት ነው። የባውሌ ህዝቦች የሚለው ቃልም መሠረት ይህ አረፍተ ነገር እንደሆነ ይነገራል። ይህ ህዝብ በዛሬይቷ አይቮሪ ኮስት ይኖራል። 

ንግሥት አብላ ፖኮው

አብላ ፖኮው በእርጥ ልጃቸውን መሥዋት አድርገዋል?
«ንግሥት አብላ ፖኮው ምናልባትም ልጃቸውን አልሰውም።» ይላሉ የታሪክ ፕሮፌሰሩ ኩአሜ ሬኔ ። 
 ለዚህም በምክንያትነት የሚያቀርቡት « በየአመቱ ለተወሰነ ጊዜያት የኮሞ ወንዝ ውኃ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ስለሚደርስ ውስጡ ያሉ ድንጋዮች ከላይ መታየት ይጀምራሉ» የሚል ነው። በርግጥም የባኤሌ ህዝቦች ያደረጉት ይህ ሊሆን ይችላል። 

አብላ ፖኮው ኮት ዲቫር ሲደርሱ የት ነው የሰፈሩት? 
ንግሥት አብላ ፖኮው ከአካዋ መንደር ብዙም ሳይርቅ በሚገኘው ብዋኬ አካባቢ ናሙኑ ውስጥ ይኖሩ ነበር። Namounou ማለት "እናታችሁን ተንከባከቡ" እንደማለት ሲሆን እዚያ ቦታ ላይ ሰፍረው የነበሩ ሰዎች አብላ ፖኮውን ይንከባከቡ እንደነበር ይነገራል።
በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ንግሥቲቱ ሲሞቶ የናሙኑ መንደር ነዋሪዎች ቦታውን ለቀው ይሄዳሉ። ንግሥቲቱም ንድራባ የተባለ ወንዝ ውስጥ እንደተቀበሩ ይነገራል።  በሳቸው ቦታ አካዋ ቦኒ የተባሉ ሳካሶ ላይ እንደሰፈሩም ይነገራል። 
ዛሬ ንግሥቲቱ እንዴት ይታወሳሉ?
ንግሥት አብላ ፖኮው ጋና እና አይቮሪ ኮስት ውስጥ አሁንም በቃልም ይሁን በፁሁፍ ይወደሳል። ይሁንና እሳቸውን የሚወክል ሰው ማግኘት ከባድ ነው።  የአቢጃን ሪፖብሊክ አደባባይ ከሚገኝ አንድ የብረት መታሠቢያ በቀር ስለ ንግሥቲቷ የሚዘክር ምንም አይነት ሙዚየምም ሆነ ሀውልት የለም። ይሁንና አንዳንድ የፋሽን ባለሙያዎች የዝነኛዋን ንግሥት አብላ ፖኮው ስም የያዙ ንድፎች ሰርተዋል።

አብላ ፖኮው

ይህ ዘገባ አፍሪካዊ ሥረ-መሠረት በሚል ከጌርዳ ሔንክል ተቋም ጋር በመተባበር የሚቀርብ ዝግጅት ነው። የዘገባው ሳይንሳዊ ምክር የተገኘው ከፕሮፌሰር ጉዳዬ ኮናቴ፣ ሊሊ ማፌላ Ph.D እና ፕሩፌሰር ክሪስቶፈር ኦግቦግቦ ነው።