ፖለቲካኔልሰን ማንዴላ፣ የአፍሪቃ ዋነኛ የጽናት ተምሳሌትTo view this video please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 videoፖለቲካ8 ነሐሴ 2010ማክሰኞ፣ ነሐሴ 8 2010ኔልሰን ማንዴላ ከአፍሪቃ ዋነኛ የጽናት ተምሳሌቶች እና ተወዳጅ የነጻነት ታጋዮች አንዱ ናቸው። የነጭ አገዛዝን እምቢኝ በማለታቸው ለሦስት ዐሥርት ዓመታት ያኽል እስር ቤት ቅቀዋል። ያም ኾኖ ግን ሠላም፣ ዲሞክራሲ እና ነጻነት ለሁሉም ሲሉ ሰብከዋል። ሀገራቸውም ከዘር መድልዎ አገዛዝ እንድትላቀቅ በመርዳት የደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያው ጥቊር ፕሬዚዳንት ኾነዋል። አንደበተ-ርቱእ፣ ትሁት እና ሆደ-ቡቡ በመኾናቸውም ይታወሳሉ። https://p.dw.com/p/33A7Oማስታወቂያ