1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ እና የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ስምምነት

ረቡዕ፣ ግንቦት 4 2013

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ እና የአፋር ሕዝብ ፓርቲ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ደረሱ። ፓርቲዎቹ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ስምምነት ካደረጉባቸው ጉዳዮች አንደኛው  ድምጽ ላለመከፋፈል መወሰናቸው ነው።

https://p.dw.com/p/3tJDB
Äthiopien Addis Abeba | Freedom and Equality Party
ምስል Yohannes G.Egziabher/DW

የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ እና የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ስምምነት

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ እና የአፋር ሕዝብ ፓርቲ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ደረሱ። ፓርቲዎቹ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ስምምነት ካደረጉባቸው ጉዳዮች አንደኛው  ድምጽ ላለመከፋፈል መወሰናቸው ነው። በዚሁ መሰረት ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ በአፋር ክልል እንደማይወዳደር አስታውቋል። በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የአፋር ህዝብ ፓርቲ ደጋፊዎች ባሉበት ድምጻቸውን ለነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ እንዲሰጡ ፓርቲዉ ጥሪ አቅርቧል።
 ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር 
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ