1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ነውጡ በብርቱ የጎዳቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች እየተረጋጉ ነው

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 4 2012

ከዚህ ሁሉ ጥፋት በኃላም ቢሆን በአብዛኞቹ የኦሮሚያ አካባቢዎች በውጥረት እንደተሞሉ የሰነበቱ ቢሆንም ያለፉትን ጥቂት ቀናት ግን ውጥረቱ አይሎ ይስተዋልባቸው የነበሩ የምስራቅ ሸዋ እና የሁለቱ አርሲ ዞኖች ረገብ እያሉ ነው።

https://p.dw.com/p/3fAAZ
Äthiopien Unruhen in Shashemene
ምስል Privat

መረጋጋት ርቋቸው የነበሩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ቀስ በቀስ እየተመሱ ነው

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል የበርክታ ሰዎችን ህይወት የነጠቀ እና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ያስከተለ ነውጥ ተከስቶ አልፏል። ከዚህ ሁሉ ጥፋት በኃላም ቢሆን በአብዛኞቹ የኦሮሚያ አካባቢዎች በውጥረት እንደተሞሉ የሰነበቱ ቢሆንም ያለፉትን ጥቂት ቀናት ግን ውጥረቱ አይሎ ይስተዋልባቸው የነበሩ የምስራቅ ሸዋ እና የሁለቱ አርሲ ዞኖች ረገብ እያሉ ነው። ከዚሁ ጎን ለጎን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ  ኮሚሽን በክልሉ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ደረሰ ያለውን ሪፖርት አቅርቧል። የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱን ወደስቱድዮ ከመግባቴ በፊት አነጋግሬው ነበር

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ