ትግራይ ውስጥ ታፍነው የነበሩ የሠራዊት አባላት
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 1 2013ማስታወቂያ
በጥቅምት 24ቱ የመቀሌው ጥቃት ታፍነው ከነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል 5000 የሚሆኑት በጎንደር በኩል ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን የክልሉ መንግሥት ባለስልጣናት አመለከቱ። የሠራዊቱ አባላት በመንገድ ብዙ ውጣውረድ ማሳለፋቸውን ይናገራሉ። ትግራይ ክልል በቆዩበት በዚህ ወቅት ስንቅ ሰጥተው የሸኟቸው እንዳሉ ሁሉ፣ በተቃራኒው ከትግራይ ልዩ ኃይል አባላት የዘረፏቸው እንዳሉ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት የገቡበት በሰሜን ጎንደር የበየዳ ወራዳ ሕዝብ ለእነሱ አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ ማድረጉም ተሰምቷል።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ