1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ ውስጥ ታስረው የተለቀቁት ጋዜጠኞች

ረቡዕ፣ የካቲት 24 2013

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ገደማ ቀናት ትግራይ ክልል ውስጥ ሁለት ጋዜጠኞችና ሁለት የውጪ መገናኛ ብዙኃን አስተርጓሚዎች ታስረው መለቀቃቸው ተሰማ።

https://p.dw.com/p/3qA2b
Äthiopien Tigray-Provinz Mekele
ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

«ጋዜጠኞችና አስተርጓሚዎች»

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ገደማ ቀናት ትግራይ ክልል ውስጥ ሁለት ጋዜጠኞችና ሁለት የውጪ መገናኛ ብዙኃን አስተርጓሚዎች ታስረው መለቀቃቸው ተሰማ። ታሳሪዎቹ ዛሬ በነጻ መለቀቃቸውን የተለያዩ የዜና አውታሮች የዘገቡ ሲሆን ከመካከላቸው አንዱ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል በገለጸው መሠረት ከመፈታታቸው በቀር በምን ምክንያት እንደተፈቱ አልተነገራቸውም። ሮይተርስ በበኩሉ ባልደረቦቻቸው የተፈቱላቸው የውጭ መገናኛ ብዙሃን በላኩለት ኢሜይል የተመሠረተባቸው ክስ የለም ማለታቸውንም ጠቅሶ ዘግቧል። ስለሁኔታው ያገኘውን መረጃ እንዲያካፍለን ከአዲስ አበባ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን ስቱዲዮ ከመግባቴ ቀደም ብዬ በስልክ ጠይቄዋለሁ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ