1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ ክልል በአቅርቦት እጥረት የተዘጉ ሐኪም ቤቶች

ረቡዕ፣ ሰኔ 15 2014

ትግራይ ክልል ውስጥ 80 በመቶ የሕክምና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆኑ ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ተገለጸ። ለሴቶች የወሊድ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ የጤና ተቋማት በውድመት አልያም የሕክምና ግብአት በማጣታቸውም ከአገልግሎት ውጭ ሆነው እናቶች ለተወሳሰበ የጤና እክል እየተዳረጉ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/4D4dl
Äthiopien | Tigray - Patient
ምስል Million Hailesilassie/DW

80 በመቶ የሕክምና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ አይደለም

ትግራይ ክልል ውስጥ 80 በመቶ የሕክምና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆኑ ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ተገለጸ። ለሴቶች የወሊድ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ የጤና ተቋማት በውድመት አልያም የሕክምና ግብአት በማጣታቸውም ከአገልግሎት ውጭ ሆነው እናቶች ለተወሳሰበ የጤና እክል እየተዳረጉ ይገኛሉ። ከጦርነቱ በፊት ከፍተኛ መቀነስ ይታይባቸው የነበሩ እንደ ፌስቱላ የመሳሰሉ በሴቶች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች ዳግም በከፋ ደረጃ እየታዩ መሆናቸውን የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል።

Äthiopien | Tigray - Hamlin Fistula
ምስል Million Hailesilassie/DW

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ብቸኛ የሆነው እና ለ16 ዓመታት በፌስቱላ መከላከያ ዙርያ መቐለ ከተማ ውስጥ አገልግሎት የሰጠው ካትሪን ሃምሊን ፌስቱላ ሕክምና ማእከል ባለፊት ዐሥር ወራት 260 የፌስቱላ ተጠቂ ሴቶች ማስተናገዱን ይገልፃል። ይህ ቁጥር ከሌሎች ዓመታት ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ከፍተኛ የተባለ መሆኑ ተነግሯል። የሕክምና ተቋማት ውድመት፣ የጤና ባለሞያዎች ፍልሰት፣ የመድኃኒት እና ሌሎች የሕክምና መገልገያ መሣርያዎች አቅርቦት እጦት ትግራይ ክልል ውስጥ የጤና ስርዓቱን ያዛቡ ምክንያቶች ሆነዋል።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ