1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትኩረት በአፍሪቃ፦ ሣዑዲ ዓረቢያ እና የአካባቢው ሃገራት

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 6 2011

ሣዑዲ ዓረቢያ ጅቡቲን ጨምሮ ከተለያዩ ሃገራት ጋር ለመሥራት እጆቿን በብዙ አቅጣጫ መዘርጋቷ የአካባቢው ጎረቤት ሃገራትን ጥቅም ያማከለ መኾኑን ጠቅሳለች። በጋር መሥራት ከተጀመረ አካባቢውን ማንም ሊያደፈርሰው እንደማይችል ተንታኞች ተናግረዋል። በአንጻሩ ሀገሪቱ የመን ላይ የከፈተችው ጦርነት ፣ እንዲሁም የኢራን ጉዳይ ከፍተኛ ተግዳሮት ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3ACG9
China Chang'e-4 Mondprogramm | Start
ምስል picture-alliance/Photoshot

ትኩረት በአፍሪቃ እና የጋዜጦች አምድ

በነዳጅ ሐብቷ የበለጸገችው ሣዑዲ ዓረቢያ ጅቡቲን ጨምሮ ከተለያዩ ሃገራት ጋር ለመሥራት እጆቿን በብዙ አቅጣጫ መዘርጋቷ የአካባቢው ጎረቤት ሃገራትን ጥቅም ያማከለ መኾኑን ጠቅሳለች። በጋር መሥራት ከተጀመረ አካባቢውን ማንም ሊያደፈርሰው እንደማይችል ተንታኞች ተናግረዋል። በአንጻሩ ሀገሪቱ የመን ላይ የከፈተችው ጦርነት ፣ እንዲሁም የኢራን ጉዳይ ከፍተኛ ተግዳሮት ነው ተብሏል።  ሣዑዲ ዓረቢያ ከ6 የቀይ ባሕር አዋሳኝ ሃገራት ጋር አብራ ለመሥራት ውሳኔ ላይ ደርሳ በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች። ኾኖም ሳዑዲ ዓረቢያ ከአካባቢው አንዳንድ ሃገራት ጋር የገባችው እሰጥ አገባ እና ጦርነት መግባቷ ከፍተኛ ተግዳሮት ነው ተብሏል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ