ትምህርትን ማዳረስ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 13 2009ማስታወቂያ
የተመ የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት በምህጻሩ የዩኔስኮ ዘገባ እና ሌሎችም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሰሀራ በስተደቡብ ባሉ የአፍሪቃ ሀገራት ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ህጻናት ቁጥር ዝቅተኛ ነው ። ትምህርት ከሚጀምሩት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአካባቢው ሀገራት ህጻናት በመምህራን እና በትምህርት መሣሪያዎች እጦት በርካቶች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸው መጨረስ አይችሉም ። አንድ መምህር እና የህክምና ባለሞያ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት በነዚህ አካባቢዎች ኢንተርኔት ብቻ በመጠቀም ትምህርትን በስፋት ማዳረስ እንደሚቻል ተናግረዋል ። ኢንተርኔትን በሚገድቡ እንደ ኢትዮጲያ ባሉ ሀገራት ደግሞ የሳተላይት ቴክኖሎጂ ትምህርትን ለማዳረስ አማራጭ መንገድ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል እኚሁ ምሁር አስረድተዋል። የዋሽንግተኑ ወኪላችን ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ