1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትምህርት እና ህይወት መሳ ለመሳ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 29 2014

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ ተወልዶ ያደገው ኩማ መርጋ በዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህብርተሰብ ጤና ሳይንስ ትምህርት ክፍል በጠቅላላ ውጤት 3.98 በማምጣት በእለቱ ምረቃ መርሀ ግብር በልዩ ማዕረግ ተመርቋል። ለኩማ ትምህርት እና ህይወት መሳ ለመሳ ሲያስኬዳቸው የነበሩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው።

https://p.dw.com/p/45GZ0
Alemaya university Medicine College graduates of 2022
ምስል Mesay Mekonnen/DW

በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ በከፍተና ማዕረግ የተመረቀችው ወጣት እና ህልማቸው

የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሰሞኑን ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል በከፍተኛ ውጤት የተመረቁት ተማሪ ኩማ መርጋ እና ተማሪ መሪቱ ለማ ይገኙበታል። በዕለቱ የወጣቶች መሰናዶአችን እንግዳ አድርገን የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን እና በቀጣይ ህይወታቸው ዙርይ ያደረግነውን ውይይት የያዘ መሰናዶ ይዘናል እንድትከታተሉን በአክብሮት እንጋብዛለን።

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ ተወልዶ ያደገው ኩማ መርጋ በዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህብርተሰብ ጤና ሳይንስ ትምህርት ክፍል በጠቅላላ ውጤት 3.98 በማምጣት በእለቱ ምረቃ መርሀ ግብር በልዩ ማዕረግ ተመርቋል። ለኩማ ትምህርት እና ህይወት መሳ ለመሳ ሲያስኬዳቸው የነበሩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው። ትምህርትን ዓላማ ይዘን ለነገ ህይወት የምንሰራበት ነው ብሏል ።

Alemaya university Medicine College graduates of 2022
ምስል Mesay Mekonnen/DW

መሪቱ ለማ በኦሮሚያ ክልል መቱ ያዮ በተባለ አካባቢ ተወልዳ ያደገች ሲሆን በኮሌጁ በአካባቢ የጤና አጠባበቅ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ 3.91 በማምጣት በከፍተኛ ውጤት ለምረቃ በቅታለች። አመታትን ባሳለፈችበት የዩኒቨርሲቲ ቆይታ ውጤት ከሰሩ ብቻ የሚመጣትበ ነው ብላለች።

መሪቱ በዩኒቨርሲቲ ቆይታ ብዙ ተመክሮዎች አግኝቼበታለሁ ብላለች።

ቀድሞም የስነ ፅሁፍ ፍላጎት ነበረኝ የሚለው ወጣት ኩማ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቆይታ ትምህርቱ ብዙም እረፍት ባይሰጥ መፅሀፍ ማሳተም መቻሉን እና  በቆይታው ከመደበኛ ትምህርት ባለፈ በተለያዩ መስኮች ባደረገው ተሳትፎ ጥሩ ጠቃሚ ግንኙነቶች መፍጠሩን ለፕሮግራማችን ገልፃል።

በ2014 ዓ.ም የምርቃ መርሀ ግብር በከፍተኛ ውጤት ለምረቃ የበቃው ወጣት ኩማ በሰለጠነበት ዘርፍ ለሀገሪቱ የበኩሉን የማበርከት ዓላማ እንዳለው በመግለፅ በሀገሪቱ በጤናው ዘርፍ ሊስተካከሉ ይገባል ያላቸውን ሀሳቦች አንስቷል።

በአካባቢ የጤና አጠባበቅ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ 3.91 በማምጣት በከፍተኛ ውጤት ለምረቃ የበቃችው መሪቱ ከጥረቷ በተጨማሪ ለስኬቴ የቤተሰቦቼ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብላለች።

መሪቱ በትልቅ ስኬት ባጠናቀቀችው የሞያ መስክ ማገልገል ፍላጎት እንዳላትም ገልፃለች።

የዕለቱ ወጣቶች ፕሮግራማችን እንግዳ ወጣት ኩማ በብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ አልፎ ዛሬ በመጀመርያው ምዕራፍ ያገኘውን ስኬት ማስቀጠል ውጥን አለው አንድ ሁለት ብሎ ምናልባት ከአስር አመት በኃላ የሚተልመው ደረጃ ትልቅ ነው።

Alemaya university Medicine College graduates of 2022
ምስል Mesay Mekonnen/DW

ከተለያየ የኑሮ ህይወት መነሻ ፣ በየምዕራፉ የሚገጥሙ ውጣ ውረዶችን አልፎ ለስኬት ለመብቃት የመጡበት መንገድ አስተማሪ መሆኑን የሚናገሩት ሁለቱ ወጣት ምሩቃን ቀጣይ ውጥናቸውም የተስፋን ትርጉም አመላካች ነው። 

በዛሬው ፕሮግራማችን ላከፈሉን ሀሳብ በማመስገን ለለቱ ያልነውን መሰናዶም እዚህ ላይ ቋጨን። ሰላም!

መሳይ ተክሉ

ነጋሽ መሐመድ