1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታሪካዊው የሸህ ሆጀሌ ችሎት አዳራሽ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 22 2013

 ሸህ ሆጀለ አሊ ሀሰን በመጀመሪያው የኢጣሊያን ወረራ ወቅት አምስት ሺህ ወታደሮችን በማሰለፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን ኢጣሊያን ዳግም ኢትጵያን ሲወርም ወደ ጦርነቱ በመዝመት በ1931 ዓ.ም ህይወታቸው ማለፉን  ከግል ታሪካቸው ያስረዳል።

https://p.dw.com/p/3yFHs
Äthiopien Kulturerbe in Assosa, Benshangul Gumuz Region, Sheh Hojele
ምስል Negassa Desalegn/DW

የታሪካዊ ቅርስ ጥበቃ

126 ዓመት ዕድሜ ያለው ታሪካዊው የሸህ ሆጀሌ  የችሎት አዳራሽ  ከህዝቡና የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በተገኘው ገንዘብ የማስዋቢያ ፕሮጀክት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።  በአሶሳ ከተማ የሚገኘው የሸህ ሆጀሌ የችሎት አዳራሽ የማስዋቢያ ፕሮጀክት በአሶሳ ከተማ አስተዳደር እና በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ሌሎት ተቋማት  የሚመራና የሚደገፍ ሲሆን እስካሁን ሦስት ሚሊዩን የሚጠጋ ገንዘብ ከመንግሥትና ከህዝብ ለግንባታው ድጋፍ መደረጉንም የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ዑመር መሐመድ ተናግረዋል። የማስዋቢያ ሥራው በአንድ ዓመት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሚሆንም ተገልጸዋል፡፡

የቤኒሻጉል ገዥ ከነበሩት ከአባታቸው ሸህ አሊሀሰን መሐመድ እና ከእናታው ወ/ሮ ፈዳይል በአሶሳ የተወለዱት ሸህ ሆጀለ የሃይማኖት ትምህርት እየተከታተሉ ያደጉና በአደን ሥራ ታዋቂ የነበሩ ሲሆን በአባታቸው የጦር መሪ ሆኖ መሾማቸውን የግል ታሪካቸውን ያስረዳል። በአሶሳ ከተማ የሚገኘው የሸህ ሆጀሌ አሊ ሀሰን የችሎት አራሽ  የሸህ ሆጀሌ  አካባቢውን  ሲያስተዳድሩ በነበሩበት ወቅት  በ1887 ዓ.ም  መገንባታቸውንና ለተለያዩ የህዝብ አስተዳደር ተግባራት ይገለገሉበት እንደነበር የሸህ ሆጀለ በተሰቦቸ መረዳጃ ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጀማል ኡመር ሆጀለ ተናግረዋል።

Äthiopien Kulturerbe in Assosa, Benshangul Gumuz Region, Sheh Hojele
ምስል Negassa Desalegn/DW

 ሸህ ሆጀለ አሊ ሀሰን በመጀመሪያው የኢጣሊያን ወረራ ወቅት አምስት ሺህ ወታደሮችን በማሰለፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን ኢጣሊያን ዳግም ኢትጵያን ሲወርም ወደ ጦርነቱ በመዝመት በ1931 ዓ.ም ህይወታቸው ማለፉን  ከግል ታሪካቸው ለማወቅ ተችሏል። በኢትዩጵያ ውስጥ ባንክ ከመመስረት ጀምሮ ሌሎች  የሸህ ሆጀሌ  ሥራዎችን በማሰባብ ላይ እንደሚገኙም አቶ ጀማ ኡመር አመልክቷል።  የሸህ ሆጀል ቤተሰቦች መረዳጃ ማህበር ለረጅም ጊዜ የጀህ ሸህ ሆጀሌ ቤተመንግሥትና  የችሎት አዳራሽ በመጠበቅ ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ሲሰራ መቆዩን አስረድተዋል። የሸህ ሆጀለ ቤተመንግሥት ወይም የችሎት አዳራሽ ተብሎ የሚታወቀው በአሶሳ የሚገኘው ታሪካዊ ቅርስ ቀዳሚውን የቱሪስት ስፋራ ለማድረግ የማስዋቢያ ሥራው እየተከናወነ ይገኛል። ከ100 ዓመት በፊት ሸህ ሆጀሌ ይገለገሉባቸው የነበሩ ሰነዶችና ቁሳቀሱችን ከተለያዩ ስፋራዎች የማሰባሰብ ሥራዎችም እየተሠሩ ነው። የችሎት አዳራሹን ጨምሮ ሸህ ሆጀሌ  በአሶሳ ከተማ ሰባት ቤቶች የነበሩአቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም ለታሪካዊ ስፋራዎቹ ጥበቃ ባመለደረጉ ሌሎቹ መፍረሳቸውን  አቶ ጀማል አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ ሸጎለ የሚገኙ የሸህ ሆጀለ አሊ ሀሰን ቤተመንግሥትም ለረዥም ጊዜያት እድሳት ሳይደረግለት በመቆየቱ የተወሰኑ ክፍሎቹ  በመጎዳታቸውንም የመፍረስ አደጋ እንዳጋጠመውም አብራርተዋል። ሙሉ ጥንቅሩን የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ