አነጋጋሪው S.3199 ረቂቅ ሕግ
ረቡዕ፣ መጋቢት 21 2014ማስታወቂያ
የዩናይትድስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነ ት ኮሚቴ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያቀረበው S 3199 የተሰኘ ረቂቅ ሕግ ማሳለፉ ምሁራንን በተለያየ ጎራ ከፍሎ እያነጋገረ ነው።
የረቂቅ ሕጉ ተቃዋሚዎች በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለማበረታታት በሚል ርዕስ የተረቀቀው ሕግ የኢትዮጵያን ኤኮኖሚ የሚጎዳና ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ብድርም ሆነ እርዳታ እንዳታገኝ የሚከለክል ነው ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።መጽደቁን የደገፉ ደግሞ ሕጉ ተጠያቂነትን ያስፍናል ሲሉ ሞግተዋል።ረቂቁ ሕግ የሚሆነዉ የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት፣የሕግ መምሪያ ምክር ቤትና ፕሬዝደንቱ ሲያፀድቁት ነዉ።
ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ