1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተስፈኛዋ ወጣት ኢትዮጵያዊት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 5 2011

ፌቨን ዘውዱ የምትኖረው እንግሊዝ ሼፈልድ ከተማ ነው። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2006፤ በ5 ዓመቷ ከኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ ከእናትቷና አክስቶቿ ጋር ተጓዘች። ፌቨን በትምህርት ቤት ቆይታዋ ምን እንደሚመስል ወደ ኋላ መለስ ብላ እንድታስታውስ ጠየኳት። በልጅነት እድሜዋ በቋንቋ መግባባት ለተወሰነ ጊዜያት ተቸግራ ነበር።

https://p.dw.com/p/3A9Zx
Großbritannien Sheffield - Feven Zewdu
ምስል Feven Zewdu

ለአገሯ ራዕይ የሰነቀች ተስፈኛ ወጣት

የእድሜ አቻ ጓደኞችም ለመያዝ አስቸጋሪ ሆኖባት እንደነበር ታስታውሳለች። ከዛ ባለፈ ፈታኝ የምትላቸው ሁኔታዎች ባይፈጠሩም በአንድ ወቅት በሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለች የተፈጠረውን ግን አትረሳውም። ስለኢትዮጵያ ድርቅ በክፍል ውስጥ ተወራ። ብቸኛ የሆነችው ሀበሻ ኢትዮጵያዊት ፌቨን ምላሽዋ ። "ቤት ገብቼ አለቀስኩ። ለአባቴ ስነግረው ስለኢትዮጵያ ጽፎ ነገ ሄደሽ አስረጃቸው አለኝ። ከዛን ቀን ጀምሮ ስለኢትዮጵያ ሲነሳ እናገራለሁ።" ስለኢትዮጵያ ማሰብ ጀመረች። ኢትዮጵያ ለሦስት ጊዜያት ያህል የሄደች ሲሆን የተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎችን ተዘዋውራ ለማየት ሞክራለች። ታሪካዊ ሀገር ሆና እያለ የህዝቦቿ የንሮ ሁኔታ እንዳሳዘናት በሌላ በኩል ትናገራለች። ፌቨን ከአደገችበት አገር ጋር ስታነጻጽረው በህብረተሰቡ መሀል መረዳዳቱ ቢኖርም ቅሉ፤ መንግስት ለህዝቡ እሳቤ እንደሌለው ትገልጻለች። ኢትዮጵያ ስትታወስና ስትጠራ ቀድሞ የሚመጣው ድህነትዋ እንጂ ቀደምት ታሪኳ አይደለም ትላለች። ፌቨን በአሁኑ ሰዓት ባዮሜዲካል እያጠናች ነው። ጋዜጠኛ የመሆን ህልም ነበራት። ሆኖም ከኢትዮጵያ መልስ ሀሳብዋን ለውጣ የህክምና ሙያን መርጣለች። ህክምና ለማጥናት ተጽኖ የፈጠረባት ኢትዮጵያ ሄዳ ከተመለሰች በሃላ እንደሆነ ትናገራለች። ለዚህም የወደፊት እቅዷን ለማሳካት ከወዲሁ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሆስፒታል ሰታለች። ውጥን እቅዷ የህክምና ትምህርቷን ተከታትላ ኢትዮጵያ ሄዳ መስራት ነው።  

 

ነጃት ኢብራሂም
እሸቴ በቀለ