1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተራድኦ ድርጅቶች በትግራይ የረሀብ አደጋ ተደቅኗል አሉ

ማክሰኞ፣ ጥር 11 2013

ወደ ትግራይ ክልል እንዳቀኑ የገለጡ ዓለም አቀፍ የርዳታ ሰጪ ተቋማት በክልሉ የምግብ እጥረት እንደተከሰተ እና የረሀብ አደጋ እንደተጋረጠ መግለጣቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/3o8St
Äthiopien Tigray-Provinz Mekele
ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

ስለትግራይ የሰብአዊ ይዞታ ከዓለም አቀፍ ተቋም

ወደ ትግራይ ክልል እንዳቀኑ የገለጡ ዓለም አቀፍ የርዳታ ሰጪ ተቋማት በክልሉ የምግብ እጥረት እንደተከሰተ እና የረሀብ አደጋ እንደተጋረጠ መግለጣቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ዶቼ ቬለ ማብራሪያ የጠየቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ በበኩሉ በተለይ ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች ለበርካታ ሳምንታት ምግብ እና መጠጥ አለማግኘታቸውን ከአካባቢው የመጡ ካላቸው ሰዎች መረጃ ማሰባሰቡን ገልጧል። አዲስ አበባ የሚገኘው የኤጀንሲው ተወካይ ጽሕፈት ቤትን የፓሪሷ ወኪላችን አነጋግራ ቀጣዩን ዘገባ ልካለች።


ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሰ