ተመላሽ ስደተኞች፣ ኢትዮጵያ እና የአውሮጳ ህብረት
ማክሰኞ፣ ጥር 22 2010ማስታወቂያ
የአውሮጳ ህብረት የተገን ጥያቄአቸው ተቀባይነት ያላገኘ ስደተኞችን ወደ የሀገራቸው መልሶ ለመላክ ከተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት ጋርም ስምምነት ላይ ደርሷል። የኢትዮጵያ መንግሥትም በአውሮጳ ህብረት አባል ሀገሮች ለመኖር ህጋዊ ፈቃድ የተከለከሉትን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መቀበል በሚችልበት ሁኔታዎች ላይ ከህብረቱ ጋር እየተደራደረ ነው። የስምምነቱ ረቂቅ ሰነድ በአንዳንድ መገናኛ ብዙሀን ይፋ ሆኖ ውይይት እና ክርክር እየተደረገበት ነው። የዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅታችን ሁለቱ ወገኖች ስለሚደራደሩበት የተመላሽ ስደተኞች ጉዳይ ስምምነት ይዘት እና አፈጻጸም ላይ ያተኩራል። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ አዘጋጅቶታል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ