1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሔራዊ መግባባት ለኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 5 2013

የጀርመን እና የአፍሪቃ ትብብር በጀርመንኛው "ዶች አፍሪቃ ሽቲፍቱንግ ፈራይን" የተሰኘው ድርጅት ኢትዮጵያውያንን እና የጀርመን ምሁራንን በጋበዘበት የውይይት መድረክ፤ ተሳታፊዎቹ መስቀለኛ መንገድ ላይ የመሚገኘው የለውጡ ሂደት እንዳይቀለበስና ፖለቲካዊ ቀውሱን ለማስወገድ፣ ሁሉን አቀፍ ውይይትና ብሄራዊ መግባባት ጠቃሚ መፍትሄ ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3jzPU
Karte Äthiopien englisch

ብሔራዊ መግባባት ለኢትዮጵያ


የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማስወገድ ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ መግባባትን የሚፈጥር ውይይት በአስቸኳይ ማካሄድ ያስፈልጋል ተባለ። የጀርመን እና የአፍሪቃ ትብብር በጀርመንኛው "ዶች አፍሪቃ ሽቲፍቱንግ ፈራይን" የተሰኘው ድርጅት ኢትዮጵያውያንን እና የጀርመን ምሁራንን በጋበዘበት የውይይት መድረክ፤ ተሳታፊዎቹ መስቀለኛ መንገድ ላይ የመሚገኘው የለውጡ ሂደት እንዳይቀለበስና ፖለቲካዊ ቀውሱን ለማስወገድ፣ ሁሉን አቀፍ ውይይትና ብሄራዊ መግባባት ጠቃሚ መፍትሄ ነው ብለዋል።የበርሊኑ የሳይንስና ፖለቲካ ጉዳዮች "ሽቲፍቱንግ ቪዝንሻፍት ኡንድ ፖሊቲክ" ድርጅት ተጠሪ ዶክተር አኔተ ቬበር፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ በለውጡ ሰሞን የነበራቸው ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ አሁን ባለው ፖለቲካዊ ቀውስ ምክንያት እያሽቆለቆለ መምጣቱን ሲገልፁ በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ወይዘሮ ሙሉ ሰለሞን ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕዝባዊ አመኔታ አሁንም ከፍ እንዳለ ነው ሲሉ ሃሳቡን ውድቅ አድርገዋል።


እንዳልካቸው ፈቃደ 


ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ