1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 170 ተጠርጣሪዎች ተፈቱ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 27 2014

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጋለሳ ቀበሌና አካባቢው ውስጥ ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ከሳምንት በፊት ታስረው ከነበሩት 300 ያህል ሰዎች መካከል በትናትናው ዕለት 170 የሚደርሱ ሰዎች መፈታታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4AssZ
Äthiopien | Assosa
ምስል Negassa Desalegn /DW

300 ያህል ሰዎች ታስረው ነበር

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጋለሳ ቀበሌና አካባቢው ውስጥ ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ከሳምንት በፊት ታስረው ከነበሩት 300 ያህል ሰዎች መካከል በትናትናው ዕለት 170 የሚደርሱ ሰዎች መፈታታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ባለፉት 3 ቀናት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በስጋት ምክንያት ተፈናቅለው በጋለሳ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ከስፍራው ማረጋገጥ ተችሏል። ከ3 መቶ ሺ በላይ ዜጎችም ከዞኑ ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኙ ቀደም ሲል ዘግበናል። ዞኑን የሚቆጣጠረው አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም። ከእንደሚገኙ ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል። 

በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ውስጥ 3 መቶ የሚደርሱ ሰዎች ከሳምንት በፊት ታስረው እንደነበር ነዋሪዎች ሲገልጹ ቆይተዋል። በወቅቱ የአካባቢውን አባገዳን ጨምሮ ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ጥርጣረ ታስሮ የነበሩ ሲሆን ግማሽ ያህሉ በትናትናው ዕለት ከበተሰባቸወ ጋር መቀላላቸውን ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። 

በድባጢ ወረዳ ጋለሳ፣ ሶምቦ ስሬ እና አምስት በሚደርሱት ቀበሌዎች ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት የኦፕረሽን ስራ እያከናወነ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን በስፍራው ባልታጠቁ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና እና በንብረት ላይም ውድመት መድረሱን ነዋሪዎች አብራርተዋል። ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ አንስቶ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከገጠር ቀበሌዎች ውስጥ መፈናቀላቸውን እና በጋለሳ ከተማ ላይ ተጠልለው እንደሚገኙ ተገልጸዋል።

የጉሙዝ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተባለ የፖለቲካ ፓርቲ በበኩሉ በዞኑ ድባጢና ቡሌን ወረዳዎች ውስጥ በርካታ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች መውደማቸው እንዲሁም በአባላቱና ሌሎችም ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ግራኝ ጉደታ ከመጋቢት 20 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ወዲህ በተለያዩ ስፍራዎች ውስጥ በነዋሪው ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። የፊታችን ሰኞ በዞኑ ሰላም ለማስፋን ያስችላል የተባለ የዕርቅና የሰላም ጉባኤ እንደሚካሄድም አክለዋል።

በድባጢ ወረዳ ያለውን ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ ከወረዳው አስተዳደር ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ጉዳዩ የዞኑን አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደርን የሚመለከት በመሆኑ እንደማይመለከተው ገልጸዋል። የዞኑ አስቸካይ ጊዜ አስተዳዳር አስተባባሪም በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም። ባለፈው አንድ ዓመት ከ7 ወራት ያህል መተከል ዞን በአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር እየተመራ የሚገኝ ሲሆን በዞኑ ሰላም ለማስፍን የደቡብ፣ የሲዳማ፣የአማራ እና ጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይሎችም በስፍራው ተሰማርተው ይገኛሉ። ከ3 መቶ ሺ በላይ ዜጎችም ከዞኑ ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኙ ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።

ነጋሣ ደሳለኝ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ