1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ «ፀረ ሰላም» የተባሉ መታሠራቸው

ሐሙስ፣ ነሐሴ 13 2013

ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 32 «ጸረ ሰላም» የተባሉ ኃይሎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። ከታሰሩት መካከልም የቤኒሻጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ(ቤ.ህ.ነ.ን) ፓርቲ አባላት እንደሚገኙበትም ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/3zB0H
Äthiopien | Gumuz region peacebuilding and security office
ምስል Negassa Dessalgen/DW

«በቁጥጥር ስር የዋሉት በሱዳን ድምበር አቅራቢያ በኩርሙክ ወረዳ ነው»

ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 32 «ጸረ ሰላም» የተባሉ ኃይሎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት በቁጥጥር ስር የዋሉት በሱዳን ድምበር አቅራቢያ በኩርሙክ ወረዳ ነው። ከታሰሩት መካከልም የቤኒሻጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ(ቤ.ህ.ነ.ን) ፓርቲ አባላት እንደሚገኙበትም ገልጸዋል።  የቤኒሻጉል ጉሙዝ ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግል ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ምላሽ ፓርቲያቸው በሰላማዊ መንገድ የሚታገል እና በምርጫ ቦርድ እውቅና ያለው መሆኑን ገልጸው፤ የቀረበውን ውንጀላ ተቃውመዋል። ጉዳዩ ፓርቲያቸውን እንደማይወክም አመልክተዋል።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ