1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቤኒ ሻንጉል እና አፋር፤ ግጭት እና ሁከት

ረቡዕ፣ ሰኔ 20 2010

ምክንያት አንድ-ዶክተር ዐብይ አሕመድ የሚመሩትን ለዉጥ ለምን ደገፋችሁ። ምክንያት ሁለት፤ ስድስት የበርታ ተወላጆች በኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) ታግተዋል-የሚል ነዉ።ሰስተኛዉ ምክንያት አንድ የከተማዉ ነዋሪ አንዳዴ ሌላ ኃይል፤ ሌላ ጊዜ TPLF የሚላቸዉ ወገኖች ያሰራጩት ቅስቀሳ ነዉ።

https://p.dw.com/p/30Q1U
Äthiopien Addis Abeba - Rally für Premierminister Abiy Ahmed
ምስል DW/G. T. Hailegiorgis

NM - MP3-Stereo

                 

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ባለፈዉ እሁድ የተጀመረዉ ግጭት እና ሁከት ዛሬም መቀጠሉን የዓይን ምስክሮች አስታወቁ። ነዋሪዎች እንደሚሉት ግጭት ሁከቱ በተለይ ርዕሠ ከተማ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ በተባለዉ ወረዳ የሰዉ ሕይወት አጥፍቷል። ግጭት ሁከቱ የተቀሰቀሰዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የሚመሩትን የለዉጥ እርምጃ በመደገፍ ሕዝብ አደባባይ በመዉጣቱ ሰበብ ነዉ ይላሉ። በአፋር መስተዳድርም ለዉጡን በመደገፍ  ሠልፍ የወጡ ተማሪዎች እና የመንግሥት ሥራተኞች ከሥራ እና ከትምሕርት ታግደዋል። ከግጭት፤ ሁከት ማባረሩ እርምጃ ጀርባ ለዉጡን የሚቃወሙ የቀድሞ ባለሥልጣናት እጅ እንዳለበት ነዋሪዎች እና የመብት ተሟጋቾች ይናገራሉ።
ቤኒ ሻንጉል! ከወርቅ፤ ግዝፍ ግድቧ በጎ ምግባርዋ እኩል፤ ባለሥልጣናትዋ አማሮችን ከማፈናቀል፤ ማሰደድ እኩይ ምግባራቸዉ ጋር ሥሟ ከስም አንሺዎች ተለይቶ አያዉቅም። አሁንም በአሳዛኝ ድርጊት አስተናጋጅነቷ ልናነሳት ተገደድን።
የማኦ ኮሞ ወረዳ ርዕሠ-ከተማ የቶንጎ ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶቹ ከአዲስ አበባ ጎንደር፤ ከደሴ፤ ደብረ ማርቆስ እንደነበረዉ ሁሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የሚመሩት የለዉጥ ኃይል እና ለዉጡን በመደገፍ አደባባ ወጡ። ቅዳሜ። ሰልፉ፤ ያዩ እንደሚሉት ሠላማዊ ነበር።
                                          
በድብደባዉ ብዙ ወጣቶች ተጎድተዋል። ብቻ  አይነጋ የለም ነጋ። እሁድ። የከተማዋ ነዋሪ ሌሊቱን የተፈፀመበትን ድብደባ በመቃወም ተሰለፈ። ሁለተኛ ቀን፤ ሁለተኛ ሰልፍ። ይኸኛዉም ሠልፍ ሰላማዊ ነበር። የአካባቢዉ ባለሥልጣናት ለድብደባዉ ይቅርታ ጠይቀዉ፤ የተደበደቡትን ለማሳከም ቃል ገብተዉ ሠልፈኛዉን አሰናበቱ። ሠልፈኛዉ ከተሰበሰበት ስታዲዮም እየጨፈረ ወደየቤቱ ሲበተን ግን ተኩስ ተከፈተበት-ምስክሩ እንደሚሉት።
                                                 
ሰወስቱ ሞቱ። ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ  ቆሰሉ። የቶንጎዉ ሁከት ቀዝቀዝ ሲል ሰኞ አሶሳ ቀጠለች። ማታ። የከተማዋ ነዋሪ እንደሚሉት ተኩሱን የከፈተዉ ፖሊስ ነዉ።
                                         
ሌላዉ የከተማይቱ ነዋሪ እንደሚሉት ሰኞ የጀመረዉ ሁከት ማክሰኞም ቀጠለ። ዛሬ ብሷል። ሰዎች ይደበደባሉ፤ ይሳደዳሉ፤ ሐብት ንብረታቸዉ ይመዘበራል።
                                    
ሕይወት፤ አካል፤ ሐብት ንብረት የሚያጠፋዉ ግጭት፤ ግድያ፤ ሁከት ምክንያት በዉል አይታወቅም። የክሉሉ መስተዳድር፤ የፖሊስ፤ እና ሆስፒታል ባለሥልጣናትን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ሥልክ ብንደዉልም አንዳንዶቹ ጋ ለስልኩ ጥሪ መልስ የሚሰጥ ሰዉ የለም። የሌሎቹ ሥልክ አይሰራም።
የአሶሳ ነዋሪዎች እንደሚሉት ግን ግጭት ሁከቱ የተነሳዉ በሰወስት ምክንያት ነዉ። ምክንያት አንድ-ዶክተር ዐብይ አሕመድ የሚመሩትን ለዉጥ ለምን ደገፋችሁ። ምክንያት ሁለት፤ ስድስት የበርታ ተወላጆች በኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) ታግተዋል-የሚል ነዉ።ሰስተኛዉ ምክንያት አንድ የከተማዉ ነዋሪ አንዳዴ ሌላ ኃይል፤ ሌላ ጊዜ TPLF የሚላቸዉ ወገኖች ያሰራጩት ቅስቀሳ ነዉ።
                                      
በአፋር መስተዳድር ለግጭት፤ ግድያ፤ ዘረፋ የደረሰ ጠብ እስካሁን የለም። ይሁንና የመንግሥት ሠራተኛ ከሥራ ገበታ፤ የኮሌጅ ተማሪዎች ከትምሕርት ታግደዋል። ሰበቡ የተድበሰበሰ ነዉ። ትክክለኛዉ ምክንያት ግን ተበደልን ባዮች እንደሚሉት ባለፈዉ ቅዳሜ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን የለዉጥ መርሕ በመደገፍ አደባባይ መዉጣታቸዉ ነዉ። ከሥራ የታገዱት የጤና ኮሌጅ መምሕር ሁሴይን ከሎይታ እንደሚሉት 
                                    
የጤና ኮሌጁ ሌሎች ሰምንት ተማሪዎችም ከትምሕርት ታግደዋል። ብራስልስ ቤልጂግ የሚኖሩት የአፋር ሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ገአስ እንደሚሉት ለዉጡን የሚደግፉ ወጣቶች በተለይ የመንግሥት ሠራተኞች ከሥራ እንባረራለን ወይም እንታሰራለን በሚል ሥጋት እየተሸማቀቁ ነዉ።
አቶ ገአስ በክልሉ የመሸጉ ያሏቸዉ የለዉጡ ተቃዋሚ ኃይላት የአፋር ወጣት እና ሕዝብ አዲስ የተጀመረዉን ለዉጥ እንዳይደግፍ እያስፈራሩት፤ እያሴሩበትም ነዉ።
                            
የአፋር ወጣቶች በሥልጣን ላይ ያለዉ መስተዳድር በሕዝብ ላይ ያደርሳል የሚሉትን በደል በመቃወም እና የታሰሩ ወገኖቻቸዉ እንዲለቀቁ በመጠየቅ ባለፉት ወራት በተለያዩ የክልሉ ከተሞች የአደባባይ ሰልፍ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚኒኬሽን ጉዳይ ሚንስትር አቶ አሕመድ ሺዴ ትናንት በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ የጀመረችዉን የለዉጥ ሒደት ለመቀልበስ የሚጥሩ ኃይላት እንዳሉ ጠቁመዋል። ሕዝቡ ለዉጡን ካደጋ ለማዳን ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጠይቀዋልም።

Äthiopien Wissenschaftlerin Forscherin Lulit Tilahun Wolde Afar Triangle
ምስል L. T. Wolde
Äthiopien Afar - Smartphone Nutzung
ምስል DW/T. Waldyes

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ