1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቤተ-እስራኤላዉያንና የሊቀ- ራባናቱ እወጃ

ሐሙስ፣ ጥር 28 2012

በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑት በቤተ እስራኤላዉያን ጉዳይ ላይ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቁት የይሁዲ እምነት ተከታይ የአቶ መስፍን አሰፋ አስተያየትም በእስራኤል ከሚኖሩት የሃይማኖቱ ተከታዮች የተለየ አይለይም። ይህን ራባኑን የሸንጎ እወጃ ቤተ እስራኤላዉያን እንዴት ተቀብለዉት ይሆን? 

https://p.dw.com/p/3XNFb
Israel Palästina Klagemauer
ምስል DW/T. Krämer

ቤተ-እስራኤላዉያንና የሊቀ ራባናቱ እወጃ

ቤተ-እስራኤላዉያንና የሊቀ- ራባናት ምክር ቤት እወጃ

የእስራኤል ሊቀ ራባናት ምክር ቤት ቤተ-እስራኤላዉያን ሙሉ በሙሉ ይሁዲዎች ናቸዉ ሲል ዉሳኔ አስተላለፈ። የምክር ቤቱ ይህ እወጃ ምን ማለት ነዉ? ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የገቡት ቤተ እስራኤላዉያን እስከዛሬ ይሁዲነታቸዉ አጠራጣሪ ነበር ማለት ነዉ? የእስራኤል ሊቀ- ራባናት ባለፈዉ ሳምንት ከኢትዮጵያ የመጡ ቤተ እስራኤልዉያን ማኅበረሰቡች ሁሉ ይሁዲዎች ናቸዉ ሲሉ ዉሳኔ አስተላልፈዋል። በእስራኤል የሚኖሩ አብዛኞች ቤተ -እስራኤላዉያን ወደ እስራኤል የመጣነዉ ዉሳኔ አግኝተን ነዉ። ይህ ለኛ ብዙ ትርጉም ባይኖረዉም በዓለም ላይ ባሉ አይሁዳዉያን ዘንድም ሆነ በሌሎች ማኅበረሰቦች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጠዋል የሚል እምነት እንዳላቸዉ ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑት በቤተ እስራኤላዉያን ጉዳይ ላይ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቁት የይሁዲ እምነት ተከታይ የአቶ መስፍን አሰፋ አስተያየትም በእስራኤል ከሚኖሩት የሃይማኖቱ ተከታዮች የተለየ አይለይም። ግን ይላሉ አቶ መስፍን ምናልባት ይህ በኢትዮጵያ የሚገኙና ወደ እስራኤል ለመሄድ ተመዝግበዉ በመጠባበቅ ላይ ያሉትን የጠቀሰ ይሆን? ይጠይቃሉ።  

በኢትዮጵያ የ 2500 ታሪክ ያለን የራሳችን ሃይማኖት ያለን ሲሉ የሚናገሩት ቤተ- እስራኤላዉያን በጥንት ዘመን በኢትዮጵያ ቁጥራቸዉ ከሦስት ሚሊዮን ይበልጥ እንደነበር ይናገራሉ።  ቅድስት ሃገር እስራኤልም ለመግባት ብዙ ዓመታት ትግል መጠየቁን የታሪክ መዛግባት ያሳያሉ። በጎርጎረሳዉያኑ 1948 ይሁዲዎች የራሳቸዉ ሃገር እስራኤልን ከመሰረቱ ወዲህ የኢትዮጵያ ይሁዲ ወደ እስራኤል ለመግባት ወደ መቶ ዓመት ትግል ማድረጋቸዉ እና ይሁንና ከእስራኤል ባስልጣን በኩል ይሁንታን አግኝተዉ ወደ ቅድስቲቱ ሃገር ለመግባት ፈተና እንደነበር ተመልክቶአል። የቤተ እስራኤላዉያኑ ወደ እስራኤል መምጣት በወቅቱ ስልጣን ላይ ለነበሩ ፖለቲከኞችም ሊዋጥላቸዉ ያልቻለ እዉነታም ነበር ተብሎአል።

በጎርጎረሳዉያን 1973 ዓ.ም ለመጀመርያ ጊዜ የይሁዲ ሃይማኖት አባት ራብ ኦባድያ ዮሴፍ ከ 400 ዓመት በፊት ያለ ታሪክን አመሳክረዉ በኢትዮጵያ የሚገኙት ቤተ እስራኤላዉያን ይሁዲ ናቸዉ ሲሉ መወሰናቸዉን ቤተ- እስራኤላዉያን ይናገራሉ። እንድያም ሆኖ በእስራኤል የሃይማኖቱ አባቶች ሁሉ ተቀባይነት ማግኘት አልቻለም ነበር ተብሎአል። ይህ ደሞ በኢትዮጵያ የሚገኙት ይሁዳዉያን ሃይማኖቱን ጠብቀዉ መኖራቸዉ ጥርጣሪ በማሳደሩ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት የእስራኤል ሊቀ-ራባናት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ የመጡ ቤተ-እስራኤልዉያን ሙሉ በሙሉ ይሁዲዎች ናቸዉ ሲል ዉሳኔ ማስተላለፉ ምን ማለት ነዉ ስንል የጠየቅናቸዉ በእስራኤል እየሩሳሉሌም የሰዎች ፀባይን የሚያጠናዉ ሶልድ በተሰኘዉ ተቋም የሚያገለግሉት አቶ ሃዋዝ ኢሳያስ ይሄ ማለት ይላሉ። የዛሬ 47 ዓመት ዉሳኔ ተሰጥቶ ፤ ቤተ እስራኤላዉያንም ወደ እስራኤል ይምጡ እንጂ ጉዳዩ በወረቅት እንጂ ተቀባይነት አልነበራቸዉም ባለት ነዉ ማለት ገቢራዊ ያልሆነ እወጃ ነበር በዝያ ጊዜም? በእስራኤል የሃይማኖቱ አባቶች በጎርጎረሳዉያኑ  1985 በሱዳን በረሃ አድርጎ ወደ እስራኤል የገባዉ የመጀመርያዉ ቤተ- እስራኤላዉያ ይሁዲነታቸዉን ሙሉ በሙሉ ባለመቀበል ያሳለፉትን ዉሳኔ ተከትሎ ቤተ እስራኤላዉያኑ እየሩሳሌም በሚገኘዉ የራባኖች ፅፈት ቤት ፊት ለፊት ከ 30 ቀናት በላይ ሌት ከቀን ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸዉ ይነገራል። ከዚህ ቀደም ሲል ወደ እስራኤል ለትምህርት ይመጡ የነበሩ ቤተ- እስራኤላዉያን ነገሩን አንስተዉ ይወተዉቱ እንደነበርም ተዘግቦአል።  ይህን ራባኑን የሸንጎ እወጃ ቤተ እስራኤላዉያን እንዴት ተቀብለዉት ይሆን? ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ