ቤተ-እስራኤላዉያን እስራኤል ገቡ
ማክሰኞ፣ ጥር 28 2011ማስታወቂያ
እስራኤል ከኢትዮጵያ የተጓዙትን ቤተ-እስራኤላውያን ሙሉ ለሙሉ እንደ አይሁድ ሳይኾን የአይሁድ ዝርያ ያላቸው አድርጋ እንደምትቆጥራቸው አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል። እስራኤል ቀሪ ቤተ-እስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ ልትወስድ ቃል ብትገባም መዘግየቷ እንዳበሳጫቸው ቤተ-እስራኤላውያኑ እና የመብት ተሟጋቾች ገልጠዋል። ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ቤተ-እስራኤላውያን በዘመቻ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የተወሰዱት ከሰላሳ ዓመታት በፊት ነበር። የእስራኤል መንግስት 82ቱን ሰዎች በዚሕ ወቅት እስራኤል እንዲገቡ መፍቀዱ ከፍትሐዊና ሰብአዊነት ይልቅ ፖለቲካዊ እድምታ አለዉ የሚል ትችት እየተሰማ ነዉ።በእስራኤል ክነሴት (ምክር ቤት) የሰዉ ኃይል አደረጃጀት የትምሕርትና ሥልጠና አስተባባሪ አቶ ዮናታን ታከለም ትችቱን ይጋራሉ።
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ