1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባሕርዳር-በረራዉ ዛሬም አልተጀመረም

እሑድ፣ ጥር 30 2013

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእና ወደ ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚያደርገዉን በረራ ዛሬም አልጀመረም።አየር መንገዱን በተለይ ከእና ወደ ላሊበላ፣ ባሕርዳርና ጎንደር የሚያደርገዉን በረራ ካለፈዉ አርብ ጀምሮ አቋርጧል።

https://p.dw.com/p/3p1Sp
Ethiopian Air Lines
ምስል Ethiopian Air Lines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእና ወደ ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚያደርገዉን በረራ ዛሬም አልጀመረም።አየር መንገዱን በተለይ ከእና ወደ ላሊበላ፣ ባሕርዳርና ጎንደር የሚያደርገዉን በረራ ካለፈዉ አርብ ጀምሮ አቋርጧል። በረራዉ ለመቋረጡ የተለያዩ ወገኖች የፀጥታ መታወክን እንደምክንያት ቢጠቅሱም አየር መንገዱ የሰጠዉ ምክንያት የአየር መበከልን ነዉ።ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ለመጓዝ ተዘጋጅተዉ የነበሩ አንዲት መንገደኛም ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን የሸፈነዉ ጭጋግ እስኪገልጥ ደረስ «ጠብቁ» መባለቸዉን አስታዉቀዋል። የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነዉ መኮንን ያነጋገራቸዉ አንድ የአየር መንገዱ ባልደረባ በበኩላቸዉ ምናልባት ነገ በረራ ሊጀመር እንደሚችል ጠቁመዋል።በኢትዮጵጵያ ሚትርዮሎጂ የባሕርዳር ቅርንጫፍ ባልደረባ ጥላሁን ዉቤ ደግሞ ባሕርዳርና አካባቢዋን ሽፍኖ የነበረዉ ጭጋግ መቀነሱን አስታዉቀዋል።ይሁንና ባለሙያዉ እንዳሉት ከሱዳን ጋር የሚዋሰኑት መተማ፣ አብደራፊና አብረሐጅራ የተባሉት አካባቢዎች አሁንም በአቧራማ ጭጋግ እንደተሸፈኑ ነዉ።

ዓለምነዉ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ