1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፈረንሳይ የኮሮናን ለመቀነስ የተወሰዱ እርምጃዎች

ዓርብ፣ መጋቢት 4 2012

በጀርመንም በተለያዩ ፌደራል ግዛቶች ከፊታችን ሰኞ አንስቶ መዋእለ-ሕጻናት እና ትምሕርት ቤቶች እንደሚዘጉ ዛሬ ተነግሯል።ፈረንሳይም ከፊታችን ሰኞ አንስቶ የትምሕርት ተቋማትን እንደምትዘጋ ዐስታውቃለች። የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ትናንት ለህዝቡ እንደተናገሩት ዐጸደ ህጻናት፣ ትምሕርት ቤቶች፣ እና ዩኒቨርስቲዎች ከሰኞ ጀምሮ ዝግ ይሆናሉ።

https://p.dw.com/p/3ZOTs
Frankreich Rede Emmanuel Macron zu Coronavirus
ምስል picture-alliance/MAXPPP/D. Thierry


የኮሮና ተህዋሲ በዓለም ዙሪያ መሰራጨቱ ቀጥሏል። የተህዋሲውን ሥርጭት ለመቀነስ የአውሮጳ መንግሥታት የተጠናከሩ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው። በርካታ ሰዎች የሚሰባሰቡባቸውን ጉባኤዎች፣ የእግር ኳስ ውድድሮች የሙዚቃ ድግሶችና የመሳሰሉትን ዝግጅቶች እየሰረዙ ትምሕርት ቤቶችንም እየዘጉ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ሠራተኞች ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩም እየተደረገ ነው። ከአውሮጳ በተህዋሲው ሥርጭት ቀዳሚውን ስፍራ በምትይዘው በኢጣልያ ትምሕርት ቤቶች ከተዘጉ ቆይተዋል። በጀርመንም በተለያዩ ፌደራል ግዛቶች ከፊታችን ሰኞ አንስቶ መዋእለ-ሕጻናት እና ትምሕርት ቤቶች እንደሚዘጉ ዛሬ ተነግሯል። ፈረንሳይም ከሚቀለው ሳምንት አንስቶ ማናቸውንም የትምሕርት ተቋማት እንደምትዘጋ ትናንት ዐስታውቃለች። የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ትናንት ለህዝቡ እንደተናገሩት ዐጸደ ህጻናት፣ ትምሕርት ቤቶች፣ እና ዩኒቨርስቲዎች ከሰኞ ጀምሮ ዝግ ይሆናሉ። በፈረንሳይ የኮሮናን ሥርጭት ለመቀነስ በመወስድ ላይ ስላሉ የጥንቃቄ ርምጃዎች የፓሪስዋን ዘጋቢያችንን አነጋግረናታል።

ሃይማኖት ጥሩነህ 

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ