በጦርነት የተጎዱ የአማራ ክልል አካባቢዎች ቅኝት
ሐሙስ፣ የካቲት 3 2014ማስታወቂያ
ከ15 ወራት በላይ የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት አሁንም በተለይ በአፋር ክልል አካባቢ መቀጠሉ ይሰማል። ለወራት የጦርነት ቀጣና ሆኖ በከረመው የአማራ ክልል ሰሜን ወሎ አንዳንድ አካባቢዎችም ዛሬም የጦርነት ስጋት መኖሩን አካባቢውን ጎብኝቶ የተመለሰው የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤ ከኅብረተሰቡ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ አጋርቶናል። ከዓለማችን አስደናቂ ቅርሶች አንዱ በሆነው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ የከፋ ጉዳት አለመድረሱን፤ ቅርሶችም አለመመዝበራቸውን ከስፍራው እንደተረዳ፤ ደሴን ጨምሮ ተዘዋውሮ በተመለከታቸው የወሎ ከተሞች ትምህርት ቤቶች ክፉኛ መጎዳታቸውንም ገልጾልናል። ጦርነቱን ለማስቆም ፖለቲካዊ መፍትሄ ሊገኝ እንደሚችል ሆኖም በኅብረተሰቡ ላይ ጦርነቱ ያስከተለው የመንፈስ ስብራት ጠግኖ የኖረውን የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ማስቀጠሉ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥቷል። ገበያውን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ ያየውን እንዲያጋራን ጠይቄዋለሁ።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ