1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጦርነቱ ለተረጂዎች የተመድ ጥያቄና የመንግስት ምላሽ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 14 2014

በኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ምክኒያት ሰለባ ለሆኑ 8 ሚሊየን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማዳረስ ማቀዱን የተመድ ሰብዓዊና አስቸኳይ ርዳታ ማስተባበሪያ ዐስታወቀ። ድርጅቱ በአማራ ክልል በሚታየዉ ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከደቡብና ሰሜን ወሎ እንዲሁም ከዋግኽምራ ዞኖች ተፈናቅለው በደብረብርሃን ከተማ መጠለላቸውን ነው ገልጿል።

https://p.dw.com/p/43Mxv
Äthiopien Bewohner des Kriegsgebiets in der Nord Wollo Zone haben Angst vor einer Hungersnot
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

የተመድ ለ 8 ሚሊየን ሕዝብ የሰብዓዊ ርዳታን ለማዳረስ አቅዶአል


እስከያዝነዉ የጎርጎጎረሳዉያን 2021 ዓመት መጨረሻ በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ምክኒያት ሰለባ ለሆኑ 8 ሚሊየን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማዳረስ ማቀዱን የተመድ ሰብዓዊና አስቸኳይ ርዳታ ማስተባበሪያ አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ በአማራ ክልል በሚታየዉ ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከደቡብና ሰሜን ወሎ እንዲሁም ከዋግኽምራ ዞኖች ተፈናቅለው በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ መጠለላቸውን ነው የገለጸው። የተመድ ሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያው ወደ ትግራይ የሚገባ ሰብዓዊ ድጋፍ ከተቋረጠ ወር ማለፉንና ከነሐሴ ጀምሮ የነዳጅ አቅርቦት መቋረጡን ገልጿል፡፡ ለሰብአዊ ድጋፍ የሚያቀርቡ ተቋማት በአፋር እና በአማራ ተደራሽ መሆን በሚችሉ አካባቢዎች ለ150 ሺህ ዜጎች የምግብ ድጋፍ ማድረጋቸውንም አክሏል። የኢትዮጵያ መንግስት በፊናው ችግሩ የሚቀርቡትን ርዳታ የማስተባበር ሳይሆን ርዳታውን ላልባለ ዓላማ የማዋል ዝንባሌ ታይቷል ሲል ይከሳል። 

ሥዩም ጌቱ  
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ