1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዝ የሆነዉ የደቡብ ክልል

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 16 2011

የደቡብ ክልል ከትናንት ምሽት ጀምሮ በፌደራል የመከላከያ ሠራዊት በሚመራ ጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) ስር አንዲመራ መወሰኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። የክልሉ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በሚል በክልሉ መንግስታዊ ቴሌቪዝን በሰበር ዜና ይፍ የተደረገው አዋጅ በተለይ በሀዋሳ ነዋሪዎች ዘንድ ተስፋም ፣ ጥርጣሬም አንዳጫረ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/3McuV
Äthiopien Ethnie der Sidama
ምስል DW/S. Wegayehu

ነዋሪዎች ኮማንድ ፖስቱን በተስፋና ጥርጣሬ ነዉ የተመለከቱት

የደቡብ ክልል ከትናንት ምሽት ጀምሮ በፌደራል የመከላከያ ሠራዊት በሚመራ ጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) ስር አንዲመራ መወሰኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። የክልሉ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በሚል በክልሉ መንግስታዊ ቴሌቪዝን በሰበር ዜና ይፍ የተደረገው አዋጅ በተለይ በሀዋሳ ነዋሪዎች ዘንድ ተስፋም ፣ ጥርጣሬም አንዳጫረ ይገኛል። አንዳንዶች መረጋጋት እየራቀው የሚገኘውን ክልል ወደ ቀደመ ሰላሙ ለመመልስ ወታደራዊ ዕዙ በጎ አስተዋጹኦ ይኖረዋል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። በአንፃሩ ሌሎች ደግሞ በአሁኑወቅት በየቦታው የሚነሱ የአስተዳድር መዋቅር ጥያቄዎችን ለማኮላሸት አስቀድሞ የታቀደ ነው በሚል በጥርጣሬ እንደሚያዩት ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት ትናንት ይፍ ያደረገው ወታደራዊ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) በሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተሞች ተፈፃሚ እንደሚሆን አስተውቋል። ወታደራዊ ዕዙ ያስፈለገው በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የለውጡን ሂደት በአግባቡ ባልተረዱ አካላት የተለያዩ ሁከትና ብጠብጦች በመከሰታቸው ነው ብሏል። ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በህጋዊና ሰላማዊ መንገዶች እንዳይመለሱ የራሳቸውን ፍላጎት መነሻ ያደረጉ ሀይሎች ህዝቡን በተሳሳተ ስሜት እየመሩት ይገኛሉ ሲል በመግለጫው አመልክቷል።  በዚህም የተነሳ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሚነሱ ሁከት ፣ ብጥብጥ ፣ ህገ ውጥነትና ዘረፋ የዜጎች ህይወትና ንብረት አደጋ ላይ እየወደቀ ይገኛል ሲል በመግለጫው ጠቁሞል። በተለይም የታጠቁ ጸረ ስላም ቡድኖች አካባቢዎችን ማወክና ያልተፈቀዱ ሰልፎች ማበራከት የሰራዊቱን አባላት ጭምር አደጋ ላይ የጣሉቡት ሁኔታ መስተዋሉን ነው በመግለጫው የዘረዘረው። የክልሉ የጸጥታ መዋቅር የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ደካማና ውጤት አልባ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ተቋማቱ በራሳቸው በአካባቢያዊ አጀንዳዎች የተተበተቡ ናቸው ሲልም ተችቷል። በመሆኑም የወታደራዊ ዕዙ በክልሉ ሰላም ጸጥታን ለማስፈን ፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲቻል ከትናንት ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን አስታውቋል።

 የክልሉ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በሚል በክልሉ መንግስታዊ ቴሌቪዝን በሰበር ዜና ይፍ የተደረገው አዋጅ በተለይ በሀዋሳ ነዋሪዎች ዘንድ ተስፋም ፣ ጥርጣሬም አንዳጫረ ይገኛል። አንዳንዶች መረጋጋት እየራቀው የሚገኘውን ክልል ወደ ቀደመ ሰላሙ ለመመልስ ወታደራዊ ዕዙ በጎ አስተዋጹኦ ይኖረዋል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል ።

በአንፃሩ ሌሎች ደግሞ በአሁኑወቅት በየቦታው የሚነሱ የአስተዳድር መዋቅር ጥያቄዎችን ለማኮላሸት አስቀድሞ የታቀደ ነው በሚል በጥርጣሬ እንደሚያዩት ገልጸዋል።

መንግስት የደቡብ ክልልን በወታደራዊ ዕዝ ( ኮማንድ ፖስት ) እነዲመራ ለማድረግ ያነሳሳው ምን ይመስሎታል በሚል በዶቼ ቨለ ( ዲ ደብሊው ) የተጠየቁት የቀድሞው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና የልማት ጥናት መምህር አቶ ሁሴን ወዮ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል። በአሁኑ ወቀት የመፍትሄው አካል ከመሆን ይልቅ የመንግስትን ምላሽ ብቻ የሚጠብቁ ጥያቄዎች እተበራከቱ መምጣት በመንግስት ላይ ጫና አየፈጠሩ ይገኛሉ የሚሉት የአስተዳደርና የልማት ጥናት ባለሙያው አቶ ሁሴን ወዮ አዋጁ የክልሉ መስተዳድር ጥያቄዎቹን ጊዜ ወስዶ ለማጤን እድል ይፈጥርለታል ብለዋል። በደቡብ ክልል ከትናንት ምሽት ጀምሮ ገቢራው የሆነው ጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) በቀጣይ የማስፈጸሚያ ደንቦች ተዘጋጅተው ለህዝብ ይፋ እንደሚደረጉ በመግለጫው ተመልክቷል ።

 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ

ተስፋለም ወልደየስ