1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመስቃን ወረዳ ግጭት የሟቾች ቁጥር 24 ደረሰ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 8 2011

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሟቾች ቁጥር 24 መድረሱ ተሰምቷል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ በ167 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአካባቢው አስተዳደር ዛሬ ለDW ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/38RRJ
Meskel Urlaubsort Äthiopien
ምስል DW/R.Kifle

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሟቾች ቁጥር 24 መድረሱ ተሰምቷል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ በ167 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአካባቢው አስተዳደር ዛሬ ለDW ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ አካላት ወደ ሥፍራው መግባታቸውን ተከትሎ ግጭቱ እየተረጋጋ መምጣቱን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በመስቃን እና በማረቆ ህዝቦች መካከል ባለፈው ረቡዕ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በመሬት ይገባኛል በተፈጠረ አለመግባባት ነበር። ግጭቱ የተከሰተበት ቦታ በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ሰሜን ዲዳ እና ባቶ ፎቶ በተባሉ ሁለት ቀበሌዎች የነበረ ሲሆን በዚህም ምክንያት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም መፈናቀላቸውን የዓይን እማኞች ለDW ተናግረዋል።

 በደቡብ ክልል መስቃን ወረዳ መሰል ግጭት ሲከሰት የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ባለፈው መስከረም በደረሰው ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እና ንብረት መውደሙ ይታወሳል። የሐዋሳው የ DW ዘጋቢ ሸዋንግዛው ወጋየሁ ያጠናቀረውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ልደት አበበ