በጅንካ ከተማና አካባቢው ጥቃት የደረሰባችው ነዋሪዎች ስጋት
ሰኞ፣ ሚያዝያ 3 2014ማስታወቂያ
በደቡብ ኦሞ ዞን በጅንካ ከተማና አካባቢው በተቀሰቀሰ ሁከት ጥቃት የደረሰባችው ነዋሪዎች አሁንም በስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ገለጹ፡፡ የጂንካ ከተማ አጎራባች በሆኑ ወረዳዎች በሺህዎች የሚገመቱ ነዋሪዎች ነፍሳቸውን ለማትረፍ በጸጥታ ተቋማት እና በቤተ ክርሰቲያናት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ዛሬ ለዶቼ ቬለ DW ተናግረዋል ፡፡
ነዋሪዎቹ አንዳሉት የአሪ ብሄር በዞን መዋቅር እንዲደራጅ የሚጠይቁ ወጣቶች ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በቀሰቀሱት ሁከት በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ፤ በርካታ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች በአሳት ወድመዋል፡፡
ሁከቱ የተቀሰቀሰው የአሪ ብሄር አክቲቪስት ነን በሚሉ ግለሰቦች ነው የሚሉት የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ አሁን ላይ አካባቢውን የማረጋጋት ሥራዎች እየተከናውኑ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ