1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣቱ ኢትዮጵያዊ መሃንዲስ ንጉስ ሃይሉ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 22 2014

ኢትዮጵያዊ መሃንዲስ ንጉስ ሃይሉ በጀርመን አሻራውን እያኖረባችው ካሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች የቦን ከለን አውሮፕላን ማረፊያ አንዱ ነው።

https://p.dw.com/p/450Pe
Äthiopischer Bauingenieur Nigus Hailu im Einsatz am Flughafen Bonn/Köln
ምስል DW

በጀርመን ሀገር የወጣቱ መሃንዲስ አሻራ

                     

በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ አፈር ፈጭቶ ጭቃ አብኩቶ እንዳደገው ሁሉጭ መሃንዲስ ንጉስ ሃይሉም እንዲያ ሆኖ ነው ያደገው። ሆኖም ግን ከሌሎች አብሮ አደጎቹ ለየት አሚያደርገው የጭቃ ቤት ሲሰራ ልክ እንደመሃንዲሶች ቤቱ የት  መሰራት እንዳለበት፣ የመጫወቻ ተሽከርካሪዎች የሚቀመጡበት ቦታና ባጠቃላይ የቤቱን ቅርጽ የሚነድፈው እሱ እንደነበር አጫውቶናል።

ውጭ ሄዶ የመማር ብዙ ፍላጎት እንዳልነበረው የሚገልጸው ወጣቱ መሃዲስ አንድ ጓደኛው ያዳመጠው የውጭ ትምህርት እድል የራድዮ ማስታወቅያ አማካይኝነት ወደ ጀርመን አገር እንዳቀና ነግሮናል።ካገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ወጣቱ መሃንዲስ ንጉስ ሃይሉ የዩንቨርስቲ ትምህርቱን ከመጀመሩ በፊት የጀርመንኛ ቋንቋን እንደተማረ አወግቶናል። ጀርመን አገር የኖሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን የጀርመኖቹ ቋንቋ መልመድ ከባድ እንደሆነ ይናገራሉ። ቋንቋውን ለመልመድ ከባድ ቢሆንም ፍላጎት ካለ ግን ከባዱን ነገር እንደሚያቀለው ይናገራል።              

ካገር ርቆ በአዲስ ባህል፣ ቋንቋ እንዲሁም የተለያየ ማህበረሰብ ጋ መኖሩ ብዙ ተነግረው የማያልቁ የህይወት ልምዶች እንዲያካብት እንደረዱት የገለጸልን ወጣቱ መሃንዲስ ንጉስ ሃይሉ በተለይ የዩንቨርስቲ ጊቢ ህይወት ጠንካራ ስባእናን እንዳላበሰው ያስታውሰዋል።

                       

የጀርመንኛ ቋንቋ፣ የጀርመኖች ባህል፣ አመጋገብና የኑሮ ዘይቤዎችን ከሃገርኛ ልምዱ ጋ እየቀመረ ንሮው በከለን ከተማ ያደረገው ኢንጅነር ንጉስ ትምህርቱን ጨርሶ በስቪል ምህንድስና ከተመረቀ ቦሃላ በተለያዩ ፕሮጀክቶች አሻራውን ማኖሩን ቀጥሏል። የስራ አለም ልምዱ በዩንቨርቲ ያገኘውን የንድፈሃሳብ ትምህርት ከተግባር ጋ አዋህዶ በመስኩ የተሻለ እውቀት እንዲኖረወው እንደረዳው ይናገራል። በመሆኑም ሙያውን የበለጠ እንዲወደው እንዳደርገው ልምዱን አጋርቶናል።

ከጊዜ ወደጊዜ በተለያዩ የሙያው ዘርፎች ልምድ እያካበተ እንደመጣ የነገርን ኢንጅነር ንጉስ ሃይሉ አሁን ደግሞ ጀርመን ውስጥ አሉ ከሚባሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች አንዱ በሆነው ፕሮጀክት ተቅጥሮ አሻራውን እያኖረ እንደሆነ አወጋን። በቦን ከለን አውሮፕላን ማረፍያ ግንባታ ፕሮጅክት የቁጥጥርና ድጋፍ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። ስራው ከፍተኛ ሃላፊነትን እሚጠይቅ ቢሆንም የተሰጠውን ሙያዊ ሃላፊነት ከጀርመናውያን ባለሙያ አጋሮቹ ጋ በመሆን እየተወጣ ይገኛል።

እንደንጉስ ሁሉ ባህል ቋንቋውን ተምረው ዩንቨርቲ በመመረቅ የተሻለ ኑሮና የአእውቀት ደርጃ የሚደርሱ እንዳሉ ሁሉ በረሃ አቋርጠው መጥተው ከእለት ጉርስ ባልዘለለ ገቢ ለያውም አገርቤት ያለን ቤተሰብ እየረዱ የሚኖሩ በርካቶች ናቸው። የጀርመንኛ ቋንቋ ማወቅ ለዩንቨርስቲ ትመህርትም ሆነ ለማንኛውም የተሻለ ንሮና እድግት ወሳኝ እንደሆነ ይናገራል ንጉስ። ብዙዎች ግን ወደስደት ሲመጡ እድሜአቸውም ገፋ ባለበት ጊዜ ስለሆነ ተምረው የተሻለ እውቀትና ስራ ለምግኘት እንደሚቸገሩ ነግሮናል።

በልጅነቱ ይመኘው በነበረውን ሙያ በመመረቁና በመስኩ በግዙፍ ፕሮጅክት ተቀጥሮ መስራቱ ከፍተኛ እርካታ እንዳገኘ የሚገልጸው ወጣቱ መሃንዲስ ንጉስ ሃይሉ እዚህ ባካበተው እውቀትና ክህሎት ወደ አገርቤት ተመልሶ ህዝቡን ለማገልገል ፍላጎት እንዳለው ገልጾልናል።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

ሽዋየ ለገሰ