1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን መዲና የሚገኙት ደመቀ መኮንን

ዓርብ፣ ኅዳር 18 2013

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን መንግስታቸዉ ስለሚወስደዉ ርምጃ ለተለያዩ መንግስታት ለማስረዳት በአዉሮጳ የጀመሩትን ዲፕሎማሲ ዘመቻ በመቀጠል ዛሬ ጀርመን መዲና በርሊን ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/3lvf9
New York | UN-Sicherheitsrat zu Krieg in Syrien | Heiko Mass, deutscher Außenminister
ምስል Getty Images/AFP/T.A. Clary

ከጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ ጋር ተገናኝተዋል

 

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን መንግስታቸዉ ስለሚወስደዉ ርምጃ ለተለያዩ መንግስታት ለማስረዳት በአዉሮጳ የጀመሩትን ዲፕሎማሲ ዘመቻ በመቀጠል ዛሬ ጀርመን መዲና በርሊን ገብተዋል። ደመቀ መኮንን ትናንት በፈረንሳ ፓሪስ ከፕሬዚዳንት አማኑኤል ማክሮን እና ሌሎች ባለስልጣናንት ከትናንት በስትያም በብራስልስ ከአዉሮጳ ኅብረት የዉጪ ጉዳይ ኃላፊ ለጆሴፍ ቦርየል ጋር ተገናኝተዉ ነበር። ዛሬ ጀርመን መዲና በርሊን ላይ የተገኙት ደመቀ መኮንን ከጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ ጋር ተገናኝተዋል።

የኢትዮጵያዉ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዛሬ ከጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሐይኮ ማስና ከመራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል አማካሪ ጋር ተነጋግረዋል።የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሐይኮ ማስ ለኢትዮጵያዊ እንግዳቸዉ እንደነገሩት ኢትዮጵያ ባሁኑ ወቅት የተኩስ አቁም ያስፈልጋታል።ግጭቱን ለማስወገድ  የአፍሪቃ ሕብረት የሚያደርገዉን ጥረት ጀርመን እንደምትደግፍም ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አስታዉቀዋል።በሕዝቡ ላይ የሚደርሰዉ መከራ እንደሚያሳዝናቸዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ጠቅሰዉ፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጣርቶ ጥፋተኞች ለፍርድ መቅረብ አለባቸዉ ብለዋል።በኢትዮጵያና ፌደራዊ መንግስትና በሕወሓት መካከል የሚደረገዉ ግጭት የብሔር መልክና ማባሕሪ መያዝ የለበትም ሲል የጀርመኑ የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር የጽሑፍ መግለቻ አዉጥቶአል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን መግለጫ ከማዉጣቱ በፊት ስለ አቶ ደመቀ መኮንን የጀርመን ጉብኝት የበርሊኑን ወኪላችንን ጠይቀነዉ ነበር ።   

 

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ