የተሰነዘረባቸው ክስ የማሸነፍ ዕድላቸውን ያጠባል ተብሏል
ረቡዕ፣ ግንቦት 9 2009ማስታወቂያ
ከተፎካካሪዎቹ መካከል ለማሸነፍ ከፍተኛ ግምት በተሰጣቸው በቀድሞዉ የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም እና በእንግሊዛዊው ዶ/ር ዴቪድ ናባሮ መካከል የቃላት ጦርነት የተቀላቀለበት ዘመቻ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ማገባደጃ በ“ኒውዮርክ ታይምስ” ጋዜጣ ላይ በዶ/ር ናባሮ አማካሪ የተሰነዘረው ክስ የዶ/ር ቴድሮስን የማሸነፍ ዕድል የሚያጠብ ነው ተብሎለታል፡፡ የካናዳው ወኪላችን በጉዳዩ ላይ ባለሙያ አነጋግሯል፡፡ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ መስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡
አክመል ነጋሽ
ተስፋለም ወልደየስ
ነጋሽ መሐመድ