የድሬዳዋው ግጭት
ሰኞ፣ ሐምሌ 30 2010ማስታወቂያ
በድሬዳዋ አስተዳደር 09 ቀበሌ ትናንት በተፈጠረ ግጭት 10 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዋና ሳጂን ባንተ ዓለም ግርማ ለዶቼቬለ እንደገለጹት ሰዎቹ የሞቱት በግጭት እና በሁከቱ ወቅት በተነሳ እሳት እና እሳቱ ባስነሳው ጭስ ታፍነው ነው። ሃላፊው ከተማዋን ወደ ቀድሞው ሁኔታዋ ለመመለስ እየተሞከረ መሆኑንም ገልጸዋል። ድሬዳዋ ዛሬ የተሻለ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አንድ የዓይን ምስክር ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ