1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

12 ሰዎች ታሰሩ 

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 16 2012

በግድያ ወንጀል ተሳትፈዋል ተብሎ የተጠረጠሩ በዳንጉር ወረዳ ከተማ ማምቡክ ዙሪያና አይፖፖ በተባለ ስፍራ 12 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ገልጸዋል፡፡  በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከከል አራቱ በአፖፖ ቀበሌ ሲሆን ስምንቱ ደግሞ በማምቡክ እንደሆነም ተነግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3VM28
Äthiopien Assosa | Polizei, Region Police | Commission gate
ምስል DW/N. Dessalegn

በዳንጉሩ ግድያ የተጠረጠሩ 12 ሰዎች ታሰሩ 

ባለፈው ታህሳስ 4 2012 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በተፈጸመው የአራት ሰዎች ግዲያ የተጠረጠሩ 12 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡በወረዳው አፖፖ በተባለ አካባቢ አንድ ግለሰብ በስልት ከተገደለ በኋላ በበቀል ስሜት የተነሳሱ ሰዎች  ባደረሱት ጥቃት ሌሎች ሶስት ሰዎች  መገደላቸውን ኮሚሽኑ ገልጻዋል፡፡በአሁኑ ጊዜ የአካባቢውን የጸጥታ ችግር በመቆጣጠር የክልልና ፌደራል ፖሊሶች ከነዋሪዎች ጋር የደረሱ ሰብሎች በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኙ ተናግሯል፡፡ ከዚህ ሌላ ባለፈው እሁድ በጉባ ወረዳ ያረንጃ በተባለ ቦታም በአንድ ግለሰብ በተከፈተ ተኩስ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት መድረሱንና  ግለሰቡን ወዲያው በቁጥጥር ስራ ማዋል መቻሉን ኮሚሽኑ ተናግሯል። 
ከሁለት ሳምንት በፊት በዳንጉር ወረዳ ውስጥ በግለሰቦች መካከል ተፈጠረ በተባለውና አራት ሰዎችን ለሞት የዳረገው  አለመግባባትን   የጸጥታ ሐይሎች በወቅቱ ባይቆጣጠሩት ኖሮ ወደ ከባድ ትርምስ ሊያመራና ከዚህ በላይ የከፋ አደጋ ሊደርስ ይችል እንደ ነበር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሐመድ አምደኒል  ዛሬ ለዲዳብሊው ገልጸዋል፡፡ በመተከል ዞን አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ ባለበት ሁኔታ ከሰሞኑ በዜጎች ህይወት መጥፋት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን  ወደ ህግ በማቅረብና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ኮሚሽኑ እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡  በግዲያ ወንጀል ተሳትፈዋል ተብሎ የተጠረጠሩ በወረዳው ከተማ ማምቡክ ዙሪያና አፖፖ በተባለ ስፍራ 12 ሰዎች  በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ገልጸዋል፡፡  በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከከል አራቱ በአፖፖ ቀበሌ ሲሆን ስምንቱ ደግሞ በማምቡክ እንደሆነም ተነግረዋል፡፡በአሁኑ ጊዜ የክልሉ ፖሊስ እና መከላከያ ሰራዊት ከህብሰረተሰቡ ጋር በመሆን  የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኙም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል፡፡ በዳንጉር እና አካባቢው  ከዚህ ቀደም በህብተሰቡ ላይ ጥቃት የፈጸሙ እና በፍርድ ቤት የሚፈለጉ አካላት ያለመያዝ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ትንኮሳዎችን በማድረስ ዜጎች ተረጋግተው እንዳይኖሩ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡እነዚህ የሚፈለጉ ተጠርጠራዎች የታጠቁና ወደ ጫካ የገቡ በመሆናቸው በቀላሉ ለመቆጣጠር አልተቻለም ብለዋል፡፡ባለፈው እሁድ ማለትም ታህሳስ 12/2012 ዓ.ም ደግሞ  በጉባ ወረዳ ያረንጃ በተባለ ቦታ በአንድ ግለሰብ በተሽከርካሪ ላይ በከፈተ ተኩስ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ግለሰቡን  ወዲያው በቁጥጥር ስራ ማዋል መቻሉን ተናግረዋል፡፡  በወረዳው  በተፈጸመው ግዲያ ምክንያት በህብረሰተቡ ዘንድ ያለውን አለመረጋጋት ለመፍታት የሚያስችል ከሀይማኖት አባቶች፣ ሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች  ጋር  ውይይት እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ