በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተቃዉሞ?
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 1 2011ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ይፈጸማሉ ያሏቸውን ግድያዎች ለመቃወም ጠይቀው ፈቃድ የተከለከሉ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ጥለው ለመውጣት በመሞከራቸው የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ተናገሩ። የአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ ጠዋት በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሚገኘው ዋናው ግቢ ጥለው የወጡ ተማሪዎች መኖራቸውን ገልጸዋል። የዓይን እማኞች እንደሚሉት ከኅዳር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ውስጥ ተቃውሞ ነበር። የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት እና ኮምዩንኬሽን ክፍል ኃላፊ አቶ ደሳለው ጌትነት ግን ተማሪዎቹ ለመውጣት ቢጠይቁም በውይይት ችግሩ መፍትሔ አግኝቷል ሲሉ ለ«DW» ተናግረዋል።
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ