በደቡብ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖች አቤቱታ
ማክሰኞ፣ የካቲት 26 2011ማስታወቂያ
በአሁኑ ወቅት አልፎ አልፎ በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር የተነሳም ወደ ቀድሞ አካባቢያቸው ለመመለስ ሥጋት እንዳደረባቸው ተፈናቃዮቹ ለዲ ደብሊው ገልጸዋል። የደቡብ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የዕርዳታ አቅርቦቱ አልፎ አልፎ በተለያዩ ምክንያቶች ከሚያጋጥመው የቀናት መዘግየት በስተቀር በተያዘው ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ ይገኛል ብሏል። ወደ ቀድሞ ቀዬያቸው ለመመለስ ያጋጠማቸውን የፀጥታ ሥጋት ለመቅረፍም ከፌደራሉ የሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር በጥምረት እየተሠራ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ አስታውቋል። ተፈናቃዮቹን እና የኮሚሽኑን የሥራ ኃላፊ ያነጋገረው የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሸዋዬ ለገሠ
ተስፋለም ወልደየስ