1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ ኢትዮጵያ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 9 2013

መነሻውን ኬንያ ያደረገ የአንበጣ መንጋ በደቡብ ክልል መከሰቱን የአካባቢው ባለ ሥልጣናት ገለጹ። ባለ ሥልጣናቱ እንዳሉት መንጋው ከሰሜን ኬንያ የተመነሳው ከባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ ወደ ክልሉ እየገባ ነው።

https://p.dw.com/p/3mvi2
Global Ideas Kenia Heuschreckenplage
ምስል picture-alliance/AP Photo/B. Curtis

«መነሻው ከኬንያ ነው»

መነሻውን ኬንያ ያደረገ የአንበጣ መንጋ በደቡብ ክልል መከሰቱን የአካባቢው ባለ ሥልጣናት ገለጹ። ባለ ሥልጣናቱ እንዳሉት መንጋው ከሰሜን ኬንያ የተመነሳው ከባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ ወደ ክልሉ እየገባ ነው። እስከ አሁንም በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ በሚገኙ 13 ቀበሌያት ውስጥ መሰፈሩም ተነግሯል። የአንበጣው መንጋ በተለይ የኦሞ ወንዝ ዳርቻን ተከትለው በመስኖ እየለሙ በሚገኙ የአዝዕርት ሰብሎችና ለግጦሽ በሚውሉ እፅዋቶች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል። የበረሃ አንበጣው ወደ አካባቢው እንደሚገባ አስቀድሞ መረጃ እንደነበራቸው የገለጹት የደቡብ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች መንጋውን የመከላከሉ ሥራ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ