1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ ኢትዮጵያ የቀጠለው ሰልፍ

ሰኞ፣ ጥቅምት 29 2014

ለሰልፈኞቹ ንግግር ያሰሙት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ «የተወረረው የአማራ እና የአፋር ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮጵያውያን ናቸው» በማለት ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/42jeY
Äthiopien | Demonstration Hawassa City gegen Rebellen und US Intervention
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ህወሃት እና ኦነግ ሸኔን የተቃወመው ሰልፍ

መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጃቸውን ህውሓት እና ኦነግ ሸኔን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ ኢትዮጵያው ውስጥ ቀጥሏል። በዛሬው ዕለትም በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል። ለሰልፈኞቹ ንግግር ያሰሙት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ «የተወረረው የአማራ እና የአፋር ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮጵያውያን ናቸው» በማለት ተናግረዋል። በ1983 ዓም የደረሰበትን ግፍ በመርሳት በኦሮሞ ህዝብ እየነገደ የሚገኘው አነግ ሸኔ አሁን ህውሓትን ወደ ቤተ መንግሥት ለማስገባት እየሠራ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይሁን እንጂ ኦነግ ሸኔ ሸኚ እንጂ ገዢ ሊሆን አይችልም ብለዋል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ