1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዓለማችን ከ 258 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት የሚሄዱበት ት/ቤት የላቸዉም

ማክሰኞ፣ ሰኔ 16 2012

በዓለም ዙርያ የሚገኙ ወደ 258 ሚሊዮን ሕጻናት ትምህርት ቤት አይሄዱም፤ አብዛኞቹ ሕጻናት የሚገኙት ከሳህራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት እና በእስያ ነዉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምሕርት፥ የሳይንስ እና የባሕል ተቋም /ዩኔስኮ/ የኮሮና የዝዉዉር ገደብ ጉዳዩን አንዳያባብሰዉ ሲል ስጋቱን ገልፆአል።

https://p.dw.com/p/3eEZZ
Namibische Jungen
ምስል picture-alliance/ZB/M. Toedt

 

በጎርጎረሳዉያን  2018  በዓለም ዙርያ የሚገኙ ወደ 258 ሚሊዮን ሕጻናት የሚሄዱበት ትምህርት ቤት የላቸዉም፤ አልያም ምንም እዉቀትን አልቀሰሙም ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምሕርት፥ የሳይንስ እና የባሕል ተቋም /ዩኔስኮ/ አስታወቀ። ይህ ቁጥር በዓለም ዉስጥ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል 17 መቶ ያህሉ መሆኑን ዩኔስኮ ገልፆል። ትምህርት ቤት ካልሄዱት 258 ሚሊዮን ሕጻናት መካከል 90 በቶዉ ደግሞ  የሚገኙት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ ሃገራት እና በእስያ መሆኑ ተመልክቶአል። ድሕነት ለትምህርት እጦት ዋንኛ ጠንቅ መሆኑን የገለፀዉ ድርጅቱ አስታዉቋል። ከድሕነት በተጨማሪ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናት እና ወጣቶች በዘር ጥላቻ እና ባለባቸዉ የአካል ጉዳት ምክንያት ትምህርት ለመቅሰም ሆነ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ አለመቻላቸዉ ሌላዉ አሳሳቢ ጉዳይ ነዉ። የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ተከትሎ በዓለም ሃገራት የወጡ የተለያዩ እገዳዎችን ተከትሎ ፤ ትምህርት ቤት የማይሄዱም ሆነ እዉቀት ለማግኘት ምንም መንገድ የሌላቸዉ  ሕጻናት እና ወጣቶች ቁጥሩ እየጨመረ ነዉ ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምሕርት፥ የሳይንስ እና የባሕል ተቋም ዩኔስኮ ባወጣዉ መግለጫ አሳስቦአል። 

 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ