1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዓለማችን በፈንጂ የሚሞተዉ ሰዉ ቁጥር ጨምሮአል

ዓርብ፣ ኅዳር 4 2013

በዓለፈዉ የጎርጎረሳዉያን  2019 ዓመት በዓለማችን 5544 ሰዎች በተቀበረ ፈንጂ ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን ዓለም አቀፉ «ሃንዲ ካፕ ኢንተርናሽናል » የተባለዉ ድርጅት አስታወቀ። በተቀበረ ጦር መሳርያ ሰበብ ከሞቱ ሰዎች መካከል 1562 ቱ ሕጻናት መሆናቸዉን «ሃንዲ ካፕ ኢንተርናሽናል » የተባለዉ ድርጅት አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/3lDDl
Jemen Landminen-Räumung
ምስል Getty Images/AFP/A. Al-Basha

በዓለፈዉ የጎርጎረሳዉያን  2019 ዓመት በዓለማችን 5544 ሰዎች በተቀበረ ፈንጂ ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን ዓለም አቀፉ «ሃንዲ ካፕ ኢንተርናሽናል » የተባለዉ ድርጅት አስታወቀ።  በጦርነት ላይም ሆነ ከጦርነት በኋላ አካባቢ ላይ በሚቀር መሳርያ ብሎም የተቀበረ ፈንጂን በማምከን የሚታወቀዉ ይህ ዓለም አቀፍ ድርጅት ዛሬ ይፋ ባደረገዉ መግለጫ በዓለማችን ከሚገኙ ሃገራት መካከል በተለይ አፍጋኒስታን፤ ሶርያ፤ ማይናመር፤ ማሊ እና ዩክሬይን ዉስጥ  ከነበረዉ ጦርነት በኋላ በፍልምያ አካባቢዎች ላይ በቀረዉ የጦር መሳርያ ቅሪት ብዙ ሰዎች ሕይወታቸዉን ያጡበት ሃገራት ናቸዉ። ባለፈዉ 2019 ዓመት ከጦርነት በኋላ በተገኘ ወይም በተቀበረ ጦር መሳርያ ሰበብ ከሞቱ ሰዎች መካከል 1562 ቱ ሕጻናት መሆናቸዉን «ሃንዲ ካፕ ኢንተርናሽናል » የተባለዉ ድርጅት አስታዉቋል። ድርጅቱ አረመኔያዊ ያለቸዉን መሳርያዎችን መጠቀምን ለማስቆም በተወዛጋቢ ወገኖች ላይ ዓለም ጫናዉን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርቦአል።