1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዎላይታ የተሰቀሰው አለመረጋጋት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 7 2012

በዎላይታ ዞን የከፍተኛ አመራሮችን አስር ተከትሎ ከባለፈው እሁድ ጀምሮ የተሰቀሰው አለመረጋጋት አሁንም አልበረደም። ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የዞኑ አመራሮች በዋስ መለቀቃቸው ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/3gurX
Äthiopien Proteste Wolita Zone
ምስል Addis Standerd

በዎላይታ የተሰቀሰው አለመረጋጋት አሁንም አልበረደም

በዎላይታ ዞን የከፍተኛ አመራሮችን አስር ተከትሎ ከባለፈው እሁድ ጀምሮ የተሰቀሰው አለመረጋጋት አሁንም አልበረደም ።
ትናንት በወላይታ ሶዶ ከተማ ከጸጥታ አባላት ተተኩሷል በተባለ ጥይት ተጨማሪ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በሌሎች ከተሞ ደግሞ አሁንም ተቃውሞና አለመረጋጋት እንደሰፈነባቸው ይገኛል። በተለይም በወላይታ ሶዶና በቦዲቲ ከተሞች የመንግስት ተቋማት ፣ ባንኮችና የንግድ ድርጅቶች አሁንም እንደተዘጉ እንደሚገኙ የየከተሞቹ ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
በአስር ላይ የሚገኙት የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ከሰዓት በኋላ በዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የታሳሪዎቹ የቅርብ ዘመዶች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል ።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 
አዜብ ታደሰ