በወንጀል ተጠርጣሪ ባለሥልጣናት
ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2011ማስታወቂያ
ወንጀለኞችን በማሳደድ ሂደት መንግሥት ጥንቃቄ እንዲያደርግ አንድ ምሁር አሳሰቡ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው በጅጅጋ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር አቶ ሙሳ አደም እንዳሉት በወንጀል የተጠረጠሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መያዝ ህዝብ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲኖረው የሚያደርግ እንደ ድልም የሚቆጠር እርምጃ ነው። ወንጀለኞችን በመያዝ ሂደት ግን ንጹሀን እንዳይጎዱ የተጠና እርምጃ መወሰድ አለበት ብለዋል። በርሳቸው አስተያየት ቁጥጥር ካልተደረገ «የደነገጠ» ያሉት ቡድን ወደ አሉታዊ መንገድ ሊሄድ ይችላል። አቶ ሙሳን ሂሩት መለሰ አነጋግራቸዋለች። አቶ ሙሳ ከአሁኑ የመንግሥት እርምጃ በኋላ ሊጠበቅ የሚችለውን እና መንግሥትም ሆነ ህዝቡ ተጠርጣሪዎችን ተጠያቂ በማድረግ ሂደት ሊከተሉ ይገባል የሚሉትን አቅጣጫ በማስረዳት ይጀምራሉ።
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ